Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 21:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እስ​ራ​ኤ​ል​ንም በተ​ገ​ዳ​ደረ ጊዜ የዳ​ዊት ወን​ድም የሴ​ማይ ልጅ ዮና​ታን ገደ​ለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እርሱም እስራኤልን በተገዳደረ ጊዜ፣ የዳዊት ወንድም የሳምዓ ልጅ ዮናታን ገደለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ይህም ሰው እስራኤልን በተገዳደረ ጊዜ፥ የዳዊት ወንድም የሻማ ልጅ ዮናታን ገደለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እርሱም እስራኤላውያንን በብርቱ ተፈታተነ፤ ይሁን እንጂ እርሱን የዳዊት ወንድም የሻማ ልጅ ዮናታን ገደለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እስራኤልንም በተገዳደረ ጊዜ የዳዊት ወንድም የሣማ ልጅ ዮናታን ገደለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 21:21
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔ ባሪ​ያህ አን​በ​ሳና ድብ ገደ​ልሁ፤ ይህም ያል​ተ​ገ​ረ​ዘው ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ ከእ​ነ​ርሱ እንደ አንዱ ይሆ​ናል። እን​ግ​ዲህ እገ​ድ​ለው ዘንድ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተግ​ዳ​ሮ​ትን አስ​ወ​ግድ ዘንድ ዛሬ አል​ሄ​ድ​ምን? የሕ​ያው አም​ላክ ጭፍ​ሮ​ችን ይገ​ዳ​ደር ዘንድ ይህ ቈላፍ ምን​ድን ነው?”


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም፥ “ዛሬ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ጭፍ​ሮች ተገ​ዳ​ደ​ር​ኋ​ቸው፤ አንድ ሰው ስጡኝ ሁለ​ታ​ች​ንም ለብ​ቻ​ችን እን​ዋጋ አል​ኋ​ቸው” አለ።


እሴ​ይም ሣማ​ዕን አሳ​ለ​ፈው፤ እር​ሱም፥ “ይህን ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​መ​ረ​ጠ​ውም” አለ።


አስ​ተ​ዋ​ይና ጸሓፊ የነ​በ​ረው በአ​ባቱ በኩል የዳ​ዊት አጎት ዮና​ታን አማ​ካሪ ነበረ፤ የአ​ክ​ማ​ኔም ልጅ ኢያ​ሔ​ኤል ከን​ጉሡ ልጆች ጋር ነበረ፤


እሴ​ይም የበ​ኵር ልጁን ኤል​ያ​ብን፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም አሚ​ና​ዳ​ብን፥ ሦስ​ተ​ኛ​ው​ንም ሣማን፥


የሐ​ማት ንጉሥ፥ የአ​ር​ፋድ ንጉሥ፥ የሴ​ፋ​ሩ​ሄም ከተማ ንጉሥ፥ የኤ​ናና የዓዋ ንጉሥ ወዴት አሉ?”


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም በአ​ንድ ወገን በተ​ራራ ላይ ቆመው ነበር፥ እስ​ራ​ኤ​ልም በሌ​ላው ወገን በተ​ራራ ላይ ቆመው ነበር፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ሸለቆ ነበረ።


ደግ​ሞም በጌት ላይ ጦር​ነት ሆነ፤ በዚ​ያም በእ​ጁና በእ​ግሩ ስድ​ስት ስድ​ስ​ት​ሁ​ላ​ሁሉ ሃያ አራት ጣቶች የነ​በ​ሩት አንድ ረዥም ሰው ነበረ፤ እርሱ ደግሞ ከራ​ፋ​ይም የተ​ወ​ለደ ነበረ።


እነ​ዚ​ያም አራቱ በጌት ውስጥ ከረ​ዐ​ይት የተ​ወ​ለዱ የራ​ፋ​ይም ወገ​ኖች ነበሩ፤ በዳ​ዊ​ትም እጅ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም እጅ ወደቁ።


ለአ​ም​ኖ​ንም የዳ​ዊት ወን​ድም የሳ​ምዓ ልጅ ኢዮ​ና​ዳብ የሚ​ባል ወዳጅ ነበ​ረው፤ ኢዮ​ና​ዳ​ብም እጅግ ብልህ ሰው ነበረ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች