2 ሳሙኤል 20:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 ሴቲቱም፥ “ኢዮአብ አንተ ነህን?” አለችው። እርሱም፥ “እኔ ነኝ” ብሎ መለሰላት። እርስዋም፥ “የባሪያህን ቃል ስማ” አለችው። ኢዮአብም፥ “እሰማለሁ” አላት። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 ኢዮአብ ወደ እርሷ ሄደ፤ እርሷም፣ “ኢዮአብ አንተ ነህ?” ስትል ጠየቀችው። እርሱም፣ “አዎን እኔ ነኝ” ብሎ መለሰላት። እርሷም፣ “እንግዲህ አገልጋይህ የምትለውን ስማ” አለችው። እርሱም፣ “ዕሺ፣ አደምጣለሁ” አላት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ኢዮአብ ወደ እርሷ ቀረበ፤ እርሷም፥ “ኢዮአብ አንተ ነህ?” ስትል ጠየቀችው። እርሱም፥ “አዎን እኔ ነኝ” ብሎ መለሰላት። እርሷም፥ “እንግዲህ አገልጋይህ የምትለውን አድምጥ” አለችው። እርሱም፥ “እያዳመጥኩ ነው” አላት። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 ኢዮአብ ወደዚያ በሄደ ጊዜም ሴትዮዋ “ኢዮአብ የምትባለው አንተ ነህን?” ስትል ጠየቀችው። እርሱም “አዎ እኔ ነኝ” አላት። እርስዋም “ጌታዬ፥ እስቲ አድምጠኝ” አለችው፤ እርሱም “እነሆ፥ አዳምጥሻለሁ” አላት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 ወደ እርስዋም ቀረበ፥ ሴቲቱም፦ ኢዮአብ አንተ ነህን? አለች። እርሱም፦ እኔ ነኝ ብሎ መለሰላት። እርስዋም፦ የባሪያህን ቃል ስማ አለችው። እርሱም፦ እሰማለሁ አላት። ምዕራፉን ተመልከት |