Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 20:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አሜ​ሳ​ይም በደም ተነ​ክሮ በመ​ን​ገድ መካ​ከል ወድቆ ነበር፤ ያም ሰው ወደ እርሱ የሚ​መጣ ሁሉ ሲቆም አይ​ቶ​አ​ልና ሕዝቡ ሁሉ እንደ ቆመ ባየ ጊዜ አሜ​ሳ​ይን ከመ​ን​ገድ ላይ ወደ እርሻ ውስጥ ፈቀቅ አደ​ረ​ገው፤ በል​ብ​ስም ከደ​ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በዚህ ጊዜ የአሜሳይ ሬሳ በደም ተጨማልቆ በመንገዱ መካከል ወድቆ ነበር፤ በዚያ የሚያልፈው ሰራዊት ሁሉ መቆሙን ያ ሰው አየ፤ ወደ ሬሳው የደረሰው ሰራዊት ሁሉ መቆሙን በተረዳ ጊዜም፣ የአሜሳይን ሬሳ ከመንገድ ወደ ዕርሻ ፈቀቅ አድርጎ ልብስ ጣል አደረገበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በዚህን ጊዜ የአማሳይ ሬሳ በደም ተጨማልቆ በመንገዱ መካከል ወድቆ ነበር፤ በዚያ የሚያልፈው ሠራዊት ሁሉ መቆሙን ያ ሰው አየ፤ ወደ ሬሳው የደረሰው ሠራዊት ሁሉ መቆሙን በተረዳ ጊዜም፥ የአማሳይን ሬሳ ከመንገድ ወደ እርሻ ፈቀቅ አድርጎ በልብስ ሸፈነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የዐማሳ ሬሳ በደም እንደ ተበከለ በመንገዱ መካከል ተዘርሮ ነበር፤ ያም ሰው የኢዮአብ ወታደር ሁሉ ቆሞ ሲመለከት አይቶ ሬሳውን በመጐተት ወደ እርሻ ወሰደውና በልብስ ሸፈነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 አሜሳይም በመንገድ መካከል ወድቆ በደሙ ላይ ይንከባለል ነበር፥ ያም ሰው ወደ እርሱ የሚመጣ ሁሉ ሲቆም አይቶአልና ሕዝቡ ሁሉ እንደ ቆመ ባየ ጊዜ አሜሳይን ከመንገድ ላይ ወደ እርሻ ውስጥ ፈቀቅ አደረገው፥ በልብስም ከደነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 20:12
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤ​ሴ​ሎ​ምም በሠ​ራ​ዊቱ ላይ በኢ​ዮ​አብ ስፍራ አሜ​ሳ​ይን ሾመ፤ አሜ​ሳ​ይም የኢ​ዮ​አ​ብን እናት የሶ​ር​ህ​ያን እኅት የነ​ዓ​ሶ​ንን ልጅ አቢ​ግ​ያን የአ​ገ​ባው የኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው የዮ​ቶር ልጅ ነበር።


ነገር ግን ከእ​ርሱ ፈቀቅ ይል ዘንድ እንቢ አለ። አበ​ኔ​ርም በጦሩ ጫፍ ወገ​ቡን ወጋው፤ ጦሩም በኋ​ላው ወጣ፤ በዚ​ያም ስፍራ ወድቆ በበ​ታቹ ሞተ። አሣ​ሄ​ልም ወድቆ በሞ​ተ​በት ስፍራ የሚ​ያ​ልፍ ሁሉ ይቆም ነበር።


ከኢ​ዮ​አ​ብም ብላ​ቴ​ኖች አንዱ በአ​ሜ​ሳይ ሬሳ አጠ​ገብ ቆሞ፥ “ኢዮ​አብ የሚ​ፈ​ል​ገው ምን​ድን ነው? የዳ​ዊ​ትም የሆኑ ኢዮ​አ​ብን የሚ​ከ​ተሉ እነ​ማን ናቸው?” አለ።


ከመ​ን​ገ​ድም ፈጥኖ ራቅ ባለ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰው ሁሉ የቢ​ኮ​ሪን ልጅ ሳቡ​ሄን ለማ​ሳ​ደድ ኢዮ​አ​ብን ተከ​ትሎ ያልፍ ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍር​ድን ማድ​ረግ ያው​ቃል፤ ኀጢ​አ​ተ​ኛው በእ​ጆቹ ሥራ ተጠ​መደ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች