Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 2:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ኢዮ​አ​ብም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ባት​ና​ገር ኖሮ ሕዝቡ ሁሉ በጥ​ዋት በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ላይ በወጡ ነበር” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ኢዮአብም፣ “ሕያው እግዚአብሔርን! ይህን ባትናገር ኖሮ፣ ሰዎቹ እስኪነጋ ድረስ ወንድሞቻቸውን ማሳደዱን ባላቆሙም ነበር” ብሎ መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ኢዮአብም፥ “ሕያው እግዚአብሔርን! ይህን ባትናገር ኖሮ፥ ሰዎቹ እስኪ ነጋ ድረስ ወንድሞቻቸውን ማሳደዱን ባላቆሙም ነበር” ብሎ መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ኢዮአብም “አንተ ይህን ቃል ባትናገር ኖሮ የእኔ ሰዎች እስከ ነገ ጠዋት ወንድሞቻቸውን ከማሳደድ እንደማይገቱ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ” ሲል መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ኢዮአብም፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ባትናገር ኖሮ ሕዝቡ በጥዋት ወጥተው በሄዱ ነበር፥ ወንድሞቻቸውንም ማሳደድ በተዉ ነበር አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 2:27
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አበ​ኔ​ርም ኢዮ​አ​ብን፥ “ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ችን ይነሡ፤ በፊ​ታ​ች​ንም ይቈ​ራ​ቈሱ” አለው፤ ኢዮ​አ​ብም፥ “ይነሡ” አለ።


አበ​ኔ​ርም ኢዮ​አ​ብን ጠርቶ እን​ዲህ አለው፥ “ሰይፍ ለድል የም​ታ​ጠፋ አይ​ደ​ለ​ምን? ፍጻ​ሜ​ዋስ መራራ እንደ ሆነ አታ​ው​ቅ​ምን? ሕዝቡ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን ከማ​ሳ​ደድ ይመ​ለሱ ዘንድ ሕዝ​ቡን የማ​ት​ና​ገር እስከ መቼ ነው?”


ኢዮ​አ​ብም ቀንደ መለ​ከት ነፋ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ተመ​ለሰ፤ ከዚ​ያም በኋላ እስ​ራ​ኤ​ልን አላ​ሳ​ደ​ዱ​አ​ቸ​ውም፤ ደግ​መ​ውም አል​ተ​ዋ​ጉም።


“እን​ደ​ዚህ የፈ​ረ​ደ​ብኝ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ነፍ​ሴ​ንም መራራ ያደ​ረገ ሁሉን የሚ​ችል ሕያው አም​ላ​ክን!


ቍጣ ጥበበኞችን ታጠፋለች፤ የለዘበ ቃል ቍጣን ይመልሳል፥ ሻካራ ቃል ግን ጠብን ያነሣሣል።


የጠብ መጀመሪያ ውኃን መድፈን ነው። የጽድቅ መጀመሪያ በነገር መሠልጠንን ይሰጣል፥ የችጋር አበጋዝ ጠብና ክርክር ነው።


ዐሳብ በምክር ትጸናለች፥ በመልካምም ምክር ሰልፍ አድርግ።


አን​ቺም፥ “እኔ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እመ​ቤት እሆ​ና​ለሁ” ብለ​ሻል፤ ይህ​ንም በል​ብሽ አላ​ሰ​ብ​ሽም፤ ፍጻ​ሜ​ው​ንም አላ​ስ​ታ​ወ​ስ​ሽም።


አሁ​ንም ጌታዬ ሆይ! ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በሕ​ያው ነፍ​ስህ እም​ላ​ለሁ! ወደ ንጹሕ ደም እን​ዳ​ት​ገ​ባና፥ እጅ​ህን እን​ድ​ታ​ድን የከ​ለ​ከ​ለህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ አሁ​ንም ጠላ​ቶ​ች​ህና በጌ​ታዬ ላይ ክፉ የሚሹ ሁሉ እንደ ናባል ይሁኑ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች