2 ሳሙኤል 19:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)40 ንጉሡም ወደ ጌልገላ ተሻገረ፤ ከመዓምም ከእርሱ ጋር ተሻገረ፤ የይሁዳም ሕዝብ ሁሉ፥ ደግሞም የእስራኤል ሕዝብ እኩሌታ ከንጉሡ ጋር ተሻገሩ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም40 ንጉሡ ወደ ጌልገላ ሲሄድ፣ ከመዓም ዐብሮት ሄደ። የይሁዳ ሰራዊት በሙሉ እንዲሁም ግማሹ የእስራኤል ሰራዊት ንጉሡን አጅበው አሻገሩት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)40 ስለዚህም ሕዝቡ በሙሉ ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ ንጉሡም ተሻገረ። ንጉሡ ባርዚላይን ስሞ መረቀው፤ ባርዚላይም ወደ ቤቱ ተመለሰ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም40 ንጉሥ ዳዊት በይሁዳ ሕዝብ ሁሉና በእስራኤል ሕዝብ እኩሌታ ታጅቦ ወንዙን ከተሻገረ በኋላ ወደ ጌልጌላ አቀና፤ ኪምሀምም አብሮት ተሻገረ፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)40 ንጉሡም ወደ ጌልገላ ተሻገረ፥ ከመዓምም ከእርሱ ጋር ሄደ፥ የይሁዳም ሕዝብ ሁሉ ደግሞም የእስራኤል ሕዝብ እኩሌታ ንጉሡን አሻገረው። ምዕራፉን ተመልከት |