Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 19:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 ሕዝ​ቡም ሁሉ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ፤ ንጉ​ሡም ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገረ፤ ንጉ​ሡም ቤር​ዜ​ሊን አቅፎ ሳመው፤ መረ​ቀ​ውም፤ ወደ ስፍ​ራ​ውም ተመ​ለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 ስለዚህም ሕዝቡ በሙሉ ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ ከዚያ በኋላም ንጉሡ ተሻገረ። ንጉሡ ቤርዜሊን ስሞ መረቀው፤ ቤርዜሊም ወደ ቤቱ ተመለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 ንጉሡም፥ “ኪምሃም ከእኔ ጋር ይሻገራል፤ አንተን ደስ የሚያሰኝህንም ሁሉ አደርግለታለሁ፤ ከእኔ የምትፈልገውን ማናቸውንም ነገር ለአንተም አደርግልሃለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 ከዚህ በኋላ ዳዊትና ተከታዮቹ ሁሉ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻገሩ፤ ዳዊትም ባርዚላይን ሳመውና ባረከው፤ ባርዚላይም ወደ ቤቱ ተመልሶ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 ሕዝቡም ሁሉ ዮርዳኖስን ተሻገረ፥ ንጉሡም ተሻገረ፥ ንጉሡም ቤርዜሊን ሳመው፥ መረቀውም፥ ወደ ስፍራውም ተመለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 19:39
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ላባም ማልዶ ተነ​ሥቶ ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶ​ችን ልጆ​ቹን ሳመ፤ ባረ​ካ​ቸ​ውም፤ ላባም ተመ​ልሶ ወደ ስፍ​ራው ሄደ።


ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው እንደ ገና አለቀሱ፣ ዖርፋም አማትዋን ሳመች፣ ሩት ግን ተጠጋቻት።


ዮሴ​ፍም ያዕ​ቆ​ብን አባ​ቱን አስ​ገ​ብቶ በፈ​ር​ዖን ፊት አቆ​መው፤ ያዕ​ቆ​ብም ፈር​ዖ​ንን ባረ​ከው።


ከወንድሞች ሁሉ ጋር በተቀደሰ አሳሳም ሰላምታ ተሰጣጡ።


ሁሉም እጅግ አለ​ቀሱ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም አን​ገ​ቱን አቅ​ፈው ሳሙት።


ስም​ዖ​ንም ባረ​ካ​ቸው፤ እና​ቱን ማር​ያ​ም​ንም እን​ዲህ አላት፤ “እነሆ፥ ይህ ሕፃን ከእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ለብ​ዙ​ዎች ለመ​ው​ደ​ቃ​ቸ​ውና ለመ​ነ​ሣ​ታ​ቸው፥ ለሚ​ቃ​ወ​ሙ​ትም ምል​ክት ይሆን ዘንድ የተ​ሠ​የመ ነው፤


ኤል​ሳ​ዕም በሬ​ዎ​ቹን ተወ፤ ኤል​ያ​ስ​ንም ተከ​ትሎ ሄደ፥ “አባ​ቴ​ንና እና​ቴን እስ​ማ​ቸው ዘንድ፥ እባ​ክህ ተወኝ፤ ከዚ​ያም በኋላ እከ​ተ​ል​ሃ​ለሁ” አለው። እር​ሱም“ሂድና ተመ​ለስ፤ ምን አድ​ር​ጌ​ል​ሃ​ለሁ?” አለው።


ኢዮ​አ​ብም ወደ ንጉሥ መጥቶ ነገ​ረው፤ አቤ​ሴ​ሎ​ም​ንም ጠራው፥ ወደ ንጉ​ሡም ገብቶ ሰገ​ደ​ለት፤ በን​ጉ​ሡም ፊት ወደ ምድር በግ​ን​ባሩ ወደቀ፤ ንጉ​ሡም አቤ​ሴ​ሎ​ምን ሳመው።


ንጉ​ሡም አቤ​ሴ​ሎ​ምን፥ “ልጄ ሆይ፥ አይ​ሆ​ንም፤ እን​ከ​ብ​ድ​ብ​ሃ​ለ​ንና ሁላ​ችን አን​ሄ​ድም” አለው። የግ​ድም አለው፤ እርሱ ግን መረ​ቀው እንጂ ለመ​ሄድ እንቢ አለ።


ዳዊ​ትም ቤተ ሰቡን ሊመ​ርቅ ተመ​ለሰ። የሳ​ኦል ልጅ ሜል​ኮ​ልም ዳዊ​ትን ለመ​ቀ​በል ወጣ​ችና ሰላ​ምታ ሰጠ​ችው፥ “ከሚ​ዘ​ፍ​ኑት አንዱ እን​ደ​ሚ​ገ​ለጥ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ሚስ​ቶች ፊት በመ​ገ​ለጡ ምንኛ የተ​ከ​በረ ነው!” አለች።


ዳዊ​ትም የሚ​ቃ​ጠ​ልና የሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕት ማሳ​ረ​ግን ከፈ​ጸመ በኋላ ሕዝ​ቡን በሰ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም መረቀ።


አሁን እን​ግ​ዲህ ከእኔ በኋላ ዘሬን እን​ዳ​ት​ነ​ቅል ከአ​ባ​ቴም ቤት ስሜን እን​ዳ​ታ​ጠ​ፋው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማል​ልኝ።”


በለ​ዓ​ምም ተነሣ፤ ተመ​ል​ሶም ወደ ስፍ​ራው ሄደ፤ ባላ​ቅም ደግሞ ወደ ቤቱ ገባ።


ያዕ​ቆ​ብም ፈር​ዖ​ንን ባረ​ከው፤ ከፈ​ር​ዖ​ንም ፊት ወጣ።


ወን​ድ​ሞ​ቹን ሁሉ ሳማ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ አለ​ቀሰ፤ ከዚ​ያም በኋላ ወን​ድ​ሞቹ ከእ​ርሱ ጋር ተጨ​ዋ​ወቱ።


አም​ላኬ ከአ​ንተ ጋር ይሂድ፤ ከፍ ከፍም ያድ​ር​ግህ፤ ይባ​ር​ክህ፤ ያብ​ዛህ፤ ብዙ ሕዝ​ብም ሁን ፤


አብ​ራ​ም​ንም ባረ​ከው፤ “አብ​ራም ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ለፈ​ጠረ ለል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ባ​ረከ ነው፤


ንጉ​ሡም፥ “ከመ​ዓም ከእኔ ጋር ይሻ​ገር፤ በፊቴ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ኝ​ንም አደ​ር​ግ​ለ​ታ​ለሁ፤ አን​ተም ከእኔ የም​ት​ሻ​ውን ነገር ሁሉ አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች