Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 19:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የይ​ሁ​ዳ​ንም ሰዎች ሁሉ ልብ እንደ አንድ ሰው ልብ አድ​ርጎ አዘ​ነ​በለ፤ ወደ ንጉ​ሡም፥ “አን​ተና ብላ​ቴ​ኖ​ችህ፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህም ሁሉ ተመ​ለሱ” ብለው ላኩ​በት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እርሱም የይሁዳን ሰዎች ልብ ሁሉ እንደ አንድ ሰው ልብ አድርጎ ማረከው፤ እነርሱም “አንተም ሰዎችህም ሁሉ ተመለሱ” ብለው ወደ ንጉሡ ላኩበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 አማሳይንም፥ ‘አንተስ የዐጥንቴ ፍላጭ፥ የሥጋዬ ቁራጭ አይደለህምን? ከአሁን ጀምሮ እስከ ሕይወትህ ፍጻሜ በኢዮአብ ምትክ የሠራዊቴ አዛዥ ባላደርግህ፥ እግዚአብሔር ክፉ ያድርግብኝ፥ ከዚህ የባሰም ያምጣብኝ’ ብላችሁ ንገሩት።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የዳዊት አነጋገር የይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ለእርሱ ታማኞች እንዲሆኑ አደረጋቸው፤ ስለዚህም ከመኳንንቱ ሁሉ ጋር ተመልሶ እንዲመጣ ላኩበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የይሁዳንም ሰዎች ሁሉ ልብ እንደ አንድ ሰው ልብ አድርጎ አዘነበለ፥ ወደ ንጉሡም ልከው፦ አንተ ከባሪያዎችህ ሁሉ ጋር ተመለስ አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 19:14
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤ​ሴ​ሎ​ምም በሠ​ራ​ዊቱ ላይ በኢ​ዮ​አብ ስፍራ አሜ​ሳ​ይን ሾመ፤ አሜ​ሳ​ይም የኢ​ዮ​አ​ብን እናት የሶ​ር​ህ​ያን እኅት የነ​ዓ​ሶ​ንን ልጅ አቢ​ግ​ያን የአ​ገ​ባው የኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው የዮ​ቶር ልጅ ነበር።


ንጉ​ሡም አሜ​ሳ​ይን፥ “የይ​ሁ​ዳን ሰዎች ሁሉ በሦ​ስት ቀን ውስጥ ጥራ​ልኝ፤ አን​ተም አብ​ረህ በዚህ ሁን” አለው።


ከአ​ሕ​ዛብ ጠብ አድ​ነኝ፤ የአ​ሕ​ዛ​ብም ራስ አድ​ር​ገህ ትሾ​መ​ኛ​ለህ፤ የማ​ላ​ው​ቀው ሕዝብ ተገ​ዛ​ልኝ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዳ​ዊት እንደ ማለ​ለት እን​ዲሁ ከእ​ርሱ ጋር ዛሬ ባላ​ደ​ርግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​በ​ኔር ይህን ያድ​ር​ግ​በት፤ ይህ​ንም ይጨ​ም​ር​በት።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገድ ሁሉ ወደ ኬብ​ሮን ወደ ዳዊት መጥ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “እኛ የአ​ጥ​ን​ትህ ፍላጭ የሥ​ጋህ ቍራጭ ነን።


ያመ​ኑ​ትም ሁሉ አንድ ልብና አን​ዲት ነፍስ ሆነው ይኖሩ ነበር፤ በው​ስ​ጣ​ቸ​ውም የሁሉ ገን​ዘብ በአ​ን​ድ​ነት ነበር እንጂ “ይህ የእኔ ገን​ዘብ ነው” የሚል አል​ነ​በ​ረም።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ወጡ፤ ማኅ​በ​ሩም ከዳን እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ፥ ከገ​ለ​ዓ​ድም ሰዎች ጋር፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መሴፋ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰ​በ​ሰቡ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች