Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 19:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እና​ንተ ወን​ድ​ሞች፥ የአ​ጥ​ንቴ ፍላ​ጭና የሥ​ጋዬ ቍራጭ ናችሁ፤ እና​ንተ ንጉ​ሡን ወደ ቤቱ ከመ​መ​ለስ ስለ​ምን ዘገ​ያ​ችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እናንተ የዐጥንቴ ፍላጭ፣ የሥጋዬ ቍራጭ ወንድሞቼ ናችሁ፤ ታዲያ ንጉሡን ለመመለስ እንዴት የመጨረሻ ሰዎች ትሆናላችሁ?’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ንጉሥ ዳዊት ወደ ካህናቱ ወደ ሳዶቅና ወደ አብያታር እንዲህ ሲል መልእክት ላከ፤ “የእስራኤል ሽማግሌዎችን እንዲህ በሏቸው አለ፤ ‘በመላው እስራኤል የሚባለው ሁሉ ለንጉሡ ባለበት የደረሰው ስለሆነ፥ ንጉሡን ወደ ቤተ መንግሥቱ ለመመለስ እንዴት የመጨረሻ ሰዎች ትሆናላችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እናንተ እኮ ለእኔ የሥጋ ዘመዶቼ ናችሁ፤ ታዲያ፥ እኔን መልሶ ለመውሰድ የመጀመሪያዎቹ በመሆን ፈንታ ስለምን የመጨረሻዎቹ ትሆናላችሁ?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እናንተ ወንድሞቼ፥ የአጥንቴ ፍላጭና የሥጋዬ ቁራጭ ናችሁ፥ እናንተ ንጉሡን ከመመለስ ስለ ምን ዘገያችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 19:12
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያን ጊዜም አዳም አለ፥ “ይህች አጥ​ንት ከአ​ጥ​ንቴ ናት፤ ሥጋ​ዋም ከሥ​ጋዬ ናት፤ እር​ስዋ ከባ​ልዋ ተገ​ኝ​ታ​ለ​ችና ሚስት ትሁ​ነኝ።”


ላባም ያዕ​ቆ​ብን፥ “በእ​ው​ነት አንተ አጥ​ንቴ ሥጋ​ዬም ነህ፤ ከእኔ ጋር ተቀ​መጥ” አለው። አንድ ወር የሚ​ያ​ህ​ልም ከእ​ርሱ ጋር ተቀ​መጠ።


እነ​ሆም፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ መጡ፤ ንጉ​ሡ​ንም፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን የይ​ሁዳ ሰዎች ለምን ሰረ​ቁህ? ንጉ​ሡ​ንም ቤተ ሰቡ​ንም ዮር​ዳ​ኖ​ስን አሻ​ገሩ። የዳ​ዊ​ትም ሰዎች ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ነበሩ” አሉት።


የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች መል​ሰው፥ “ንጉሡ ለእኛ ቅር​ባ​ችን ነው፤ ስለ​ምን በዚህ ነገር ትቈ​ጣ​ላ​ችሁ? በውኑ ከን​ጉሡ አን​ዳች በል​ተ​ና​ልን? ወይስ እርሱ በረ​ከት ሰጥ​ቶ​ና​ልን? ወይስ ጭፍራ አድ​ርጎ ሾመ​ንን?” አሉ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገድ ሁሉ ወደ ኬብ​ሮን ወደ ዳዊት መጥ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “እኛ የአ​ጥ​ን​ትህ ፍላጭ የሥ​ጋህ ቍራጭ ነን።


የአ​ኪ​ጦ​ብም ልጅ ሳዶቅ፥ የአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክም ልጅ አብ​ያ​ታር ካህ​ናት ነበሩ። አሳም ጸሓፊ ነበረ፤


ይህም በዚህ ዘመ​ዶ​ችን አስ​ቀ​ና​ቸው እንደ ሆነ፥ ከእ​ነ​ርሱ ወገን የሆ​ኑ​ት​ንም አድን እንደ ሆነ ነው።


እኛ የአ​ካሉ ሕዋ​ሳት ነንና።


“ለሰ​ቂማ ሰዎች ሁሉ፦ ሰባ የሆ​ኑት የይ​ሩ​በ​ኣል ልጆች ሁሉ ቢገ​ዙ​አ​ችሁ ወይስ አንድ ሰው ቢገ​ዛ​ችሁ ምን ይሻ​ላ​ች​ኋል? ብላ​ችሁ ንገ​ሩ​አ​ቸው፤ ደግ​ሞም እኔ የአ​ጥ​ን​ታ​ችሁ ፍላጭ፥ የሥ​ጋ​ችሁ ቍራጭ እንደ ሆንሁ አስቡ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች