Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 19:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ንጉሡ ዳዊ​ትም ለካ​ህ​ናቱ ለሳ​ዶ​ቅና ለአ​ብ​ያ​ታር ልኮ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ለይ​ሁዳ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች እን​ዲህ ብላ​ችሁ ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው፦ የእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ነገር ወደ ንጉሡ ደር​ሶ​አ​ልና ንጉ​ሡን ወደ ቤቱ ከመ​መ​ለስ ስለ​ምን ዘገ​ያ​ችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ንጉሥ ዳዊት ወደ ካህናቱ ወደ ሳዶቅና ወደ አብያታር እንዲህ ሲል መልእክት ላከ፤ “የይሁዳ ሽማግሌዎችን እንዲህ በሏቸው አለ፤ ‘በመላው እስራኤል የሚባለው ሁሉ ለንጉሡ ባለበት የደረሰው ስለ ሆነ፣ ንጉሡን ወደ ቤተ መንግሥቱ ለመመለስ እንዴት የመጨረሻ ሰዎች ትሆናላችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በላያችን ሆኖ እንዲገዛን የቀባነው አቤሴሎም ደግሞ በጦርነት ሞቷል፤ ታዲያ ስለ ንጉሡ የመመለስ ጉዳይ ለምንድን ነው ዝም የምትሉት?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ንጉሥ ዳዊትም እስራኤላውያን እርስ በርሳቸው የተናገሩትን ሰማ፤ ስለዚህም ካህናቱን ሳዶቅንና አብያታርን በመላክ የይሁዳን መሪዎች እንዲህ ብለው እንዲጠይቁአቸው አዘዘ፤ “ንጉሡን ረድታችሁ ወደ ቤተ መንግሥቱ ለመመለስ ስለምን እናንተ የመጨረሻዎቹ ትሆናላችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ንጉሡም ዳዊት ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር ልኮ እንዲህ አላቸው፦ ለይሁዳ ሽማግሌዎች እንዲህ ብላችሁ ተናገሩአቸው፦ የእስራኤል ሁሉ ነገር ወደ ንጉሡ ደርሶአልና ንጉሡን ወደ ቤቱ ከመመለስ ስለ ምን ዘገያችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 19:11
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሳዶ​ቅና አብ​ያ​ታ​ርም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መለ​ሷት፤ በዚ​ያም ተቀ​መጡ።


ኢዮ​አ​ብም፥ “እኔ ከአ​ንተ ጋር እን​ዲህ እዘ​ገይ ዘንድ አል​ች​ልም” ብሎ ሦስት ጦሮች በእጁ ወሰደ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም ገና በዛፍ ላይ ተን​ጠ​ል​ጥሎ ሕያው ሳለ በልቡ ላይ ተከ​ላ​ቸው።


ዐሥ​ሩም የኢ​ዮ​አብ ጋሻ ጃግ​ሬ​ዎች ከበ​ቡት፤ አቤ​ሴ​ሎ​ም​ንም መት​ተው ገደ​ሉት።


በላ​ያ​ችን ላይ የቀ​ባ​ነው አቤ​ሴ​ሎ​ምም በጦ​ር​ነት ሞቶ​አል፤ አሁ​ንም ንጉ​ሡን ለመ​መ​ለስ ስለ​ምን ዝም ትላ​ላ​ችሁ?” አሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቃል ወደ ንጉሥ ደረሰ።


እነ​ሆም፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ መጡ፤ ንጉ​ሡ​ንም፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን የይ​ሁዳ ሰዎች ለምን ሰረ​ቁህ? ንጉ​ሡ​ንም ቤተ ሰቡ​ንም ዮር​ዳ​ኖ​ስን አሻ​ገሩ። የዳ​ዊ​ትም ሰዎች ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ነበሩ” አሉት።


ንጉ​ሡም በእ​ርሱ ፋንታ የዮ​ዳ​ሄን ልጅ በን​ያ​ስን የሠ​ራ​ዊቱ አለቃ አድ​ርጎ ሾመ፤ መን​ግ​ሥ​ቱም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጸናች። በአ​ብ​ያ​ታ​ርም ፋንታ ካህ​ኑን ሳዶ​ቅን ሾመ።


መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።


እኛስ በክ​ር​ስ​ቶስ አም​ሳል እን​ለ​ም​ና​ለን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእኛ መጽ​ና​ና​ትን ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጋር ትታ​ረቁ ዘንድ በክ​ር​ስ​ቶስ እን​ለ​ም​ና​ች​ኋ​ለን።


ይህም እኛን ልትመስሉ ራሳችንን እንደ ምሳሌ እንሰጣችሁ ዘንድ ነበር እንጂ፥ ያለ ሥልጣን ስለ ሆንን አይደለም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች