Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 18:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ንጉ​ሡም፥ “ብላ​ቴ​ናው አቤ​ሴ​ሎም ደኅና ነውን?” አለ። አኪ​ማ​ሖ​ስም፥ “ኢዮ​አብ እኔን ባሪ​ያ​ህ​ንና የን​ጉ​ሡን ባሪያ በላከ ጊዜ ብዙ ሰዎ​ችን አይ​ቻ​ለሁ፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላ​ወ​ቅ​ሁም” ብሎ መለ​ሰ​ለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ንጉሡም፣ “ብላቴናው አቤሴሎም ደኅና ነውን?” ሲል ጠየቀ። አኪማአስም፣ “ኢዮአብ የንጉሡን አገልጋይና እኔንም ባሪያህን ሊልክ ሲል፣ ትልቅ ሁካታ አይቻለሁ፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላወቅሁም” ብሎ መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ንጉሡም፥ “ወጣቱ አቤሴሎም ደኅና ነውን?” ሲል ጠየቀ። አሒማዓጽም፥ “ኢዮአብ የንጉሡን አገልጋይና እኔንም አገልጋይህን ሊልክ ሲል፥ ትልቅ ሁካታ አይቻለሁ፤ ምን እንደሆነ ግን አላወቅሁም” ብሎ መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ንጉሡም “ወጣቱ አቤሴሎም ምንም ጒዳት አልደረሰበትምን?” ሲል ጠየቀ። አሒማዓጽም “ጌታዬ ሆይ፥ የጦር አዛዥህ ኢዮአብ ወደ አንተ በላከኝ ጊዜ ታላቅ ሁካታ ሆኖ አየሁ፤ ነገር ግን ምን እንደ ሆነ መናገር አልችልም” ሲል መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ንጉሡም፦ ብላቴናው አቤሴሎም ደህና ነውን? አለ። አኪማአስም፦ ኢዮአብ እኔን ባሪያህንና የንጉሡን ባሪያ በላከ ጊዜ ትልቅ ሽብር አይቻለሁ፥ ምን እንደሆነ ግን አላወቅሁም ብሎ መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 18:29
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳግ​መ​ኛም የሳ​ዶቅ ልጅ አኪ​ማ​ሖስ ኢዮ​አ​ብን፥ “የሆነ ሆኖ ኩሲን ተከ​ትዬ፥ እባ​ክህ ልሩጥ” አለው። ኢዮ​አ​ብም፥ “ልጄ ሆይ፥ ለምን ትሮ​ጣ​ለህ? ተመ​ለስ፤ ብት​ሄድ ይች ወሬ ለጥ​ቅም አት​ሆ​ን​ህ​ምና” አለ።


ንጉ​ሡም፥ “ፈቀቅ ብለህ ቁም” አለ፤ እር​ሱም ፈቀቅ ብሎ ቆመ።


ንጉ​ሡም ኩሲን፥ “ብላ​ቴ​ናው አቤ​ሴ​ሎም ደኅና ነውን?” አለው። ኩሲም፥ “የጌ​ታዬ የን​ጉሡ ጠላ​ቶች፥ በክ​ፉም የተ​ነ​ሡ​ብህ ሁሉ እን​ደ​ዚያ ብላ​ቴና ይሁኑ” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


ኢዮ​አ​ብም አሜ​ሳ​ይን፥ “ወን​ድሜ ሆይ፥ ደኅና ነህን?” አለው፤ ኢዮ​አ​ብም አሜ​ሳ​ይን የሚ​ስም መስሎ በቀኝ እጁ ጢሙን ያዘው።


አሁ​ንም ሩጥና ተቀ​በ​ላት፤ በደ​ኅ​ናሽ ነውን? ባልሽ ደኅና ነውን? ልጅ​ሽስ ደኅና ነውን? በላት” አለው። እር​ስ​ዋም፥ “ደኅና ነው” አለች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች