Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 18:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እር​ሱም፥ “እኔ ብሮጥ ምን ይገ​ድ​ዳል?” አለ። እር​ሱም፥ “ሩጥ” አለው። አኪ​ማ​ሖ​ስም በሰ​ርጥ ጎዳና በኩል ሮጠ፤ ኩሲ​ንም ቀደ​መው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 አኪማአስም፣ “የመጣው ይምጣ፤ መሄድ እፈልጋለሁ” አለ። ስለዚህም ኢዮአብ፣ “እንግዲያውማ ሩጥ!” አለው። ከዚያም አኪማአስ በሜዳው መንገድ ሮጦ ኢትዮጵያዊውን ቀድሞት ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 አሒማዓጽም፥ “የመጣው ይምጣ፤ መሄድ እፈልጋለሁ” አለ። ስለዚህም ኢዮአብ፥ “ሩጥ!” አለው። ከዚያም አሒማዓጽ በሜዳው መንገድ ሮጦ ኢትዮጵያዊውን ቀድሞት ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 አሒማዓጽም እንደገና “የፈለገው ነገር ቢሆን ግድ የለኝም፤ እኔ መሄድ እፈልጋለሁ” አለ። ኢዮአብም “እንግዲያውስ ሂድ” አለው፤ ስለዚህም አሒማዓጽ በዮርዳኖስ ሸለቆ በሚያመራው መንገድ ሲሮጥ ሄዶ ወዲያውኑ ኢትዮጵያዊውን ቀደመው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እርሱም፦ እኔ ብሮጥ ምን ይገድዳል? አለ። እርሱም፦ ሩጥ አለው። አኪማአስም በሜዳው መንገድ በኩል ሮጠ፥ ኵሲንም ቀደመው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 18:23
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢዮ​አ​ብም ኩሲን፥ “ሂድ፤ ያየ​ኸ​ው​ንም ሁሉ ለን​ጉሥ ንገር” አለው። ኩሲም ለኢ​ዮ​አብ ሰግዶ ወጣ።


ዳግ​መ​ኛም የሳ​ዶቅ ልጅ አኪ​ማ​ሖስ ኢዮ​አ​ብን፥ “የሆነ ሆኖ ኩሲን ተከ​ትዬ፥ እባ​ክህ ልሩጥ” አለው። ኢዮ​አ​ብም፥ “ልጄ ሆይ፥ ለምን ትሮ​ጣ​ለህ? ተመ​ለስ፤ ብት​ሄድ ይች ወሬ ለጥ​ቅም አት​ሆ​ን​ህ​ምና” አለ።


ዳዊ​ትም በሁ​ለት በር መካ​ከል ተቀ​ምጦ ነበር፤ ዘበ​ኛ​ውም በቅ​ጥሩ ላይ ወዳ​ለው ወደ በሩ ሰገ​ነት ወጣ፤ ዐይ​ኑ​ንም አቅ​ንቶ ብቻ​ውን የሚ​ሮጥ ሰው አየ።


ሁለ​ቱም በአ​ን​ድ​ነት ሲሮጡ ያ ሌላዉ ደቀ መዝ​ሙር ጴጥ​ሮ​ስን ቀድ​ሞት ወደ መቃ​ብሩ ደረሰ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች