Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 17:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 አኪ​ጦ​ፌ​ልም ምክሩ እን​ዳ​ል​ሠራ ባየ ጊዜ አህ​ያ​ውን ጫነ፤ ተነ​ሥ​ቶም ወደ ቤቱ ወደ ከተ​ማው ሄደ፤ ቤቱ​ንም አደ​ራ​ጅቶ በገዛ እጁ ታንቆ ሞተ፤ በአ​ባ​ቱም መቃ​ብር ተቀ​በረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 አኪጦፌልም ምክሩን እንዳልተከተሉት ባየ ጊዜ፣ አህያውን ጭኖ ቤቱ ወደሚገኝበት ወደ መኖሪያ ከተማው ሄደ፤ ቤቱንም መልክ መልክ ካስያዘ በኋላ በገዛ እጁ ታንቆ ሞተ። በዚህ ሁኔታም ሞቶ በአባቱ መቃብር ተቀበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 አኪጦፌልም ምክሩን እንዳልተከተሉት ባየ ጊዜ፥ አህያውን ጭኖ ቤቱ ወደሚገኝበት ወደ መኖሪያ ከተማው ሄደ፤ ቤቱንም አስተካክሎ በገዛ እጁ ታነቀ፤ ከሞተ በኋላ በአባቱም መቃብር ተቀበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 አኪጦፌል የሰጠው ምክር ተቀባይነት እንዳላገኘ በተረዳ ጊዜ አህያውን ጭኖ ወደ መኖሪያ ከተማው ተመልሶ ሄደ፤ ሁሉን ነገር መልክ በማስያዝ ካስተካከለም በኋላ ተሰቅሎ ሞተ፤ በቤተሰቡም መቃብር ተቀበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 አኪጦፌልም ምክሩን እንዳልተከተሉ ባየ ጊዜ አህያውን ጫነ፥ ተነሥቶም ወደ ቤቱ ወደ ከተማው ሄደ፥ ቤቱንም አደራጅቶ በገዛ እጁ ታንቆ ሞተ፥ በአባቱም መቃብር ተቀበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 17:23
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና ታንቆ ሞተ።


በዚ​ያም ወራት ሕዝ​ቅ​ያስ ታመመ፤ ለሞ​ትም ደረሰ። ነቢ​ዩም የአ​ሞጽ ልጅ ኢሳ​ይ​ያስ ወደ እርሱ መጥቶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ በሕ​ይ​ወት አት​ኖ​ር​ምና ቤት​ህን አስ​ተ​ካ​ክል” አለው።


አቤ​ሴ​ሎ​ምም መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሠ​ዋ​በት ጊዜ የዳ​ዊት አማ​ካሪ ወደ ነበ​ረው ጌሎ​ና​ዊው አኪ​ጦ​ፌል ወደ ከተ​ማው ጊሎ ላከ። ሴራ​ውም ጽኑ ሆነ፤ ከአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምም ጋር ያለው ሕዝብ እጅግ በዛ።


አቤቱ፥ ፍረ​ድ​ባ​ቸው፥ በነ​ገረ ሠሪ​ነ​ታ​ቸ​ውም ይው​ደቁ፤ እንደ ሐሰ​ታ​ቸ​ውም ብዛት አሳ​ድ​ዳ​ቸው፥ አቤቱ፥ እነ​ርሱ አሳ​ዝ​ነ​ው​ሃ​ልና።


ዘም​ሪም ከተ​ማ​ዪቱ እንደ ተያ​ዘች ባየ ጊዜ ወደ ንጉሡ ቤት ግንብ ውስጥ ገባ፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ቤት በራሱ ላይ በእ​ሳት አቃ​ጠለ፤ ሞተም።


አኪ​ጦ​ፌል ከአ​ቤ​ሴ​ሎም ጋር በሴራ አንድ ነው ብለው ለዳ​ዊት ነገ​ሩት፤ ዳዊ​ትም፥ “አቤቱ የአ​ኪ​ጦ​ፌ​ልን ምክር ለውጥ” አለ።


የሰው ስንፍናው መንገዱን ያጣምምበታል፥ በልቡም እግዚአብሔርን ገፋኢ ያደርገዋል።


ከጥል በፊት ስድብ ይቀድማል፥ ከመውደቅም በፊት ክፋትን ማወቅ።


ሞት ለዐ​መ​ፀኛ፥ መለ​የ​ትም ኀጢ​አ​ትን ለሚ​ሠሩ ነው።


በእ​ነ​ዚያ በመ​ጀ​መ​ሪያ ወራት የመ​ከ​ራት የአ​ኪ​ጦ​ፌል ምክር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እንደ መጠ​የቅ ነበ​ረች፤ የአ​ኪ​ጦ​ፌ​ልም ምክር ሁሉ ከዳ​ዊ​ትና ከአ​ቤ​ሴ​ሎም ጋር እን​ዲሁ ነበ​ረች።


ዳዊ​ትና ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ሁሉ ተነ​ሥ​ተው ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ፤ እስ​ኪ​ነ​ጋም ድረስ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ሳይ​ሻ​ገር አንድ ሰው እን​ኳን አል​ቀ​ረም።


በዚ​ያም ወራት ሕዝ​ቅ​ያስ ለሞት እስ​ኪ​ደ​ርስ ታመመ። ነቢ​ዩም የአ​ሞጽ ልጅ ኢሳ​ይ​ያስ ወደ እርሱ መጥቶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ በሕ​ይ​ወት አት​ኖ​ር​ምና ቤት​ህን አስ​ተ​ካ​ክል” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች