Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 17:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ዳዊ​ትና ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ሁሉ ተነ​ሥ​ተው ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ፤ እስ​ኪ​ነ​ጋም ድረስ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ሳይ​ሻ​ገር አንድ ሰው እን​ኳን አል​ቀ​ረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ስለዚህ ዳዊትና ዐብሮት ያለው ሕዝብ በሙሉ ተነሥቶ ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ ሲነጋም ዮርዳኖስን ሳይሻገር የቀረ አንድም ሰው አልነበረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ስለዚህ ዳዊትና አብሮት ያለው ሕዝብ በሙሉ ተነሥቶ ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ ሲነጋም ዮርዳኖስን ሳይሻገር የቀረ አንድም ሰው አልነበረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ስለዚህም ዳዊትና ተከታዮቹ የዮርዳኖስን ወንዝ መሻገር ጀመሩ፤ እስኪነጋም ድረስ ሁሉም ወንዙን ተሻግረው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ዳዊትና ከእርሱም ጋር የነበሩት ሁሉ ተነሥተው ዮርዳኖስን ተሻገሩ፥ እስኪነጋም ድረስ ዮርዳኖስን ሳይሻገር አንድ ሰው እንኳ አልቀረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 17:22
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህም፥ “ከእ​ነ​ዚህ ከሰ​ጠ​ኸኝ አንድ ስንኳ አል​ጠ​ፋም” ያለው ቃሉ ይፈ​ጸም ዘንድ ነው።


“እነሆ እኔ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።


ዳዊ​ትም ወደ ምና​ሄም መጣ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም፥ ከእ​ርሱ ጋር የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሁሉ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ።


“ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ወደ ሰልፍ የወ​ጡ​ትን ከእ​ጃ​ችን በታች ያሉ​ትን ቈጠሩ፤ ከእ​ኛም አንድ አል​ጐ​ደ​ለም።


ከሄ​ዱም በኋላ እነ​ርሱ ከጕ​ድ​ጓዱ ወጥ​ተው ሄዱ፤ ለን​ጉ​ሡም ለዳ​ዊት ነገ​ሩት፤ ዳዊ​ት​ንም፥ “አኪ​ጦ​ፌል በእ​ና​ንተ ላይ እን​ዲህ መክ​ሮ​አ​ልና ተነሡ፤ ፈጥ​ና​ች​ሁም ውኃ​ውን ተሻ​ገሩ” አሉት።


አኪ​ጦ​ፌ​ልም ምክሩ እን​ዳ​ል​ሠራ ባየ ጊዜ አህ​ያ​ውን ጫነ፤ ተነ​ሥ​ቶም ወደ ቤቱ ወደ ከተ​ማው ሄደ፤ ቤቱ​ንም አደ​ራ​ጅቶ በገዛ እጁ ታንቆ ሞተ፤ በአ​ባ​ቱም መቃ​ብር ተቀ​በረ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች