Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 15:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 አኪ​ጦ​ፌል ከአ​ቤ​ሴ​ሎም ጋር በሴራ አንድ ነው ብለው ለዳ​ዊት ነገ​ሩት፤ ዳዊ​ትም፥ “አቤቱ የአ​ኪ​ጦ​ፌ​ልን ምክር ለውጥ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 በዚህ ጊዜ፣ “ከአቤሴሎም ጋራ ካሤሩት መካከል አንዱ አኪጦፌል ነው” ብለው ለዳዊት ነገሩት። ስለዚህ ዳዊት፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህን የአኪጦፌልን ምክር ወደ ከንቱነት ለውጠው” ብሎ ጸለየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 በዚህ ጊዜ፥ “ከአቤሴሎም ጋር ካሤሩት መካከል አንዱ አኪጦፌል ነው” ብለው ለዳዊት ነገሩት። ዳዊትም፥ “ጌታ ሆይ! እባክህን የአኪጦፌልን ምክር ወደ ከንቱነት ለውጠው” ሲል ጸለየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ዳዊት፥ አኪጦፌል ከአቤሴሎም ጋር በዐመፅ መተባበሩን በሰማ ጊዜ “እግዚአብሔር ሆይ! የአኪጦፌልን ምክር ወደ ከንቱነት እንድትለውጥበት እለምንሃለሁ!” ሲል ጸለየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 አኪጦፌል ከአቤሴሎም ጋር በሴራ አንድ ነው ብለው ለዳዊት ነገሩት፥ ዳዊትም፦ አቤቱ፥ የአኪጦፌልን ምክር ስንፍና አድርገህ እንድትለውጥ እለምንሃለሁ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 15:31
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤ​ሴ​ሎ​ምም መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሠ​ዋ​በት ጊዜ የዳ​ዊት አማ​ካሪ ወደ ነበ​ረው ጌሎ​ና​ዊው አኪ​ጦ​ፌል ወደ ከተ​ማው ጊሎ ላከ። ሴራ​ውም ጽኑ ሆነ፤ ከአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምም ጋር ያለው ሕዝብ እጅግ በዛ።


በእ​ነ​ዚያ በመ​ጀ​መ​ሪያ ወራት የመ​ከ​ራት የአ​ኪ​ጦ​ፌል ምክር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እንደ መጠ​የቅ ነበ​ረች፤ የአ​ኪ​ጦ​ፌ​ልም ምክር ሁሉ ከዳ​ዊ​ትና ከአ​ቤ​ሴ​ሎም ጋር እን​ዲሁ ነበ​ረች።


አቤ​ሴ​ሎ​ምና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ “የአ​ር​ካ​ዊው የኩሲ ምክር ከአ​ኪ​ጢ​ፌል ምክር ይሻ​ላል” አሉ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ቤ​ሴ​ሎም ላይ ክፉ ያመጣ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​ካ​ሚ​ቱን የአ​ኪ​ጦ​ፌ​ልን ምክር እን​ዲ​በ​ትን አዘዘ።


አኪ​ጦ​ፌ​ልም ምክሩ እን​ዳ​ል​ሠራ ባየ ጊዜ አህ​ያ​ውን ጫነ፤ ተነ​ሥ​ቶም ወደ ቤቱ ወደ ከተ​ማው ሄደ፤ ቤቱ​ንም አደ​ራ​ጅቶ በገዛ እጁ ታንቆ ሞተ፤ በአ​ባ​ቱም መቃ​ብር ተቀ​በረ።


አቤ​ሴ​ሎ​ምም፥ “አር​ካ​ዊ​ውን ኩሲን ጥሩት፤ ደግ​ሞም እርሱ የሚ​ለ​ውን እን​ስማ” አለ።


ኩሲም አቤ​ሴ​ሎ​ምን አለው፥ “አኪ​ጦ​ፌል በዚህ ጊዜ የመ​ከ​ራት ምክር መል​ካም አይ​ደ​ለ​ችም። ይች​ውም አን​ዲት ናት።”


የተ​ን​ኰ​ለ​ኞ​ችን ምክር ይለ​ው​ጣል፥ እጆ​ቻ​ቸ​ውም ቅን አይ​ሠ​ሩም።


ቀዳ​ማዊ፦ በኀ​ይል ቀን፥ በቅ​ዱ​ሳን ብር​ሃን ከአ​ንተ ጋር ነበር፥ ከአ​ጥ​ቢያ ኮከብ አስ​ቀ​ድሞ ከሆድ ወለ​ድ​ሁህ።


አቤቱ፥ የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁኝ ምንኛ በዙ! በእኔ ላይ የሚ​ቆ​ሙት ብዙ ናቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ሁት፥ “አንተ አም​ላኬ ነህ፤ ለምን ረሳ​ኸኝ? ጠላ​ቶቼ ሲያ​ስ​ጨ​ን​ቁኝ ለምን ተው​ኸኝ? ለም​ንስ አዝኜ እመ​ለ​ሳ​ለሁ?” ጠላ​ቶቼ ሁሉ አጥ​ን​ቶ​ቼን እየ​ቀ​ለ​ጣ​ጠሙ ሰደ​ቡኝ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃሌን አከ​ብ​ራ​ለሁ፤ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይከ​ብ​ራል።


አቤቱ፥ የም​ስ​ጋና ስእ​ለት የም​ሰ​ጥህ ከእኔ ዘንድ ነው፤


የግ​ብ​ፅም መን​ፈስ በው​ስ​ጣ​ቸው ትደ​ነ​ግ​ጣ​ለች፤ ምክ​ራ​ቸ​ውን አጠ​ፋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ ድም​ፃ​ቸ​ውን ዝቅ አድ​ር​ገው የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይጠ​ይ​ቃሉ።


በሟ​ርት ሙት እና​ስ​ነ​ሣ​ለን የሚ​ሉ​ትን፥ ከል​ባ​ቸ​ውም አን​ቅ​ተው ሐሰት የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን ሰዎች ምል​ክት የሚ​ለ​ውጥ ማን ነው? ጥበ​በ​ኞ​ቹ​ንም ወደ ኋላ ይመ​ል​ሳል፤ ምክ​ራ​ቸ​ው​ንም ስን​ፍና ያደ​ር​ጋል።


ነገር ግን ይህን የም​ና​ገር ስለ ሁላ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ የመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸው እነ​ማን እንደ ሆኑ እኔ አው​ቃ​ለሁ፤ ነገር ግን መጽ​ሐፍ ‘እን​ጀ​ራ​ዬን የሚ​መ​ገብ ተረ​ከ​ዙን በእኔ ላይ አነሣ’ ያለው ይፈ​ጸም ዘንድ ነው።


እን​ግ​ዲህ ጥበ​በኛ ማን ነው? ጸሓ​ፊስ ማን ነው? ይህን ዓለ​ምስ የሚ​መ​ረ​ም​ረው ማን ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዚ​ህን ዓለም ጥበብ ስን​ፍና አላ​ደ​ረ​ገ​ው​ምን?


ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፤ ነገር ግን የምድር ነው፤ የሥጋም ነው፤ የአጋንንትም ነው፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች