Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 15:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ሀገ​ሪ​ቱም ሁላ በታ​ላቅ ድምፅ አለ​ቀ​ሰች። ሕዝ​ቡም ሁሉ በቄ​ድ​ሮን ወንዝ ተሻ​ገሩ፤ ንጉ​ሡም ደግሞ የቄ​ድ​ሮ​ንን ወንዝ ተሻ​ገረ፤ ንጉ​ሡና ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ ምድረ በዳ በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ተሻ​ገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ሕዝቡ ሁሉ በሚያልፍበትም ጊዜ ባላገሩ በሙሉ እየጮኸ አለቀሰ፤ ንጉሡም የቄድሮንን ሸለቆ ተሻገረ፤ ሕዝቡም ሁሉ ተሻግሮ ወደ ምድረ በዳው ተጓዘ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ሕዝቡ ሁሉ በሚያልፍበትም ጊዜ ባላገሩ በሙሉ እየጮኸ አለቀሰ፤ ንጉሡም የቄድሮንን ወንዝ ተሻገረ፤ ሕዝቡም ሁሉ ተሻግሮ ወደ ምድረ በዳው አመሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 የዳዊት ተከታዮች ወጥተው በሄዱ ጊዜ ሕዝቡ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ ንጉሡ ከተከታዮቹ ጋር የቄድሮንን ወንዝ ተሻገረ፤ በአንድነትም ሆነው ወደ በረሓው አመሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 በአገርም የነበሩት ሁሉ በታላቅ ድምፅ አለቀሱ፥ ሕዝቡም ሁሉ ተሻገሩ፥ ንጉሡም ደግሞ የቄድሮንን ፈፋ ተሻገረ፥ ሕዝቡም ሁሉ ወደ ምድረ በዳ መንገድ ተሻገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 15:23
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉ​ሡም ሲባን፥ “ይህ ለአ​ንተ ምን​ድን ነው?” አለው። ሲባም፥ “አህ​ዮቹ የን​ጉሥ ቤተ ሰቦች ይቀ​መ​ጡ​ባ​ቸው ዘንድ፥ እን​ጀ​ራ​ውና ተም​ሩም ብላ​ቴ​ኖቹ ይበ​ሉት ዘንድ፥ የወ​ይን ጠጁም በበ​ረሃ የሚ​ደ​ክ​ሙት ይጠ​ጡት ዘንድ ነው” አለ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ተና​ግሮ አት​ክ​ልት ወደ አለ​በት ስፍራ ወደ ቄድ​ሮስ ወንዝ ማዶ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ወጣ፤ ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ጋር ወደ​ዚያ ገባ።


በም​ት​ወ​ጣ​በ​ትና የቄ​ድ​ሮ​ን​ንም ፈፋ በም​ት​ሻ​ገ​ር​በት ቀን ፈጽ​መህ እን​ደ​ም​ት​ሞት ዕወቅ፤ ደም​ህም በራ​ስህ ላይ ይሆ​ናል።” ያን​ጊ​ዜም ንጉሡ አማ​ለው።


ደስ ከሚ​ለው ጋር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ከሚ​ያ​ለ​ቅ​ሰው ጋርም አል​ቅሱ።


ሕፃ​ኑም አደገ፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም ጸና፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም እስ​ከ​ታ​የ​በት ቀን ድረስ በም​ድረ በዳ ኖረ።


በነቢዩ በኢሳይያስ “ ‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ ጥርጊያውንም አቅኑ’ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ” የተባለለት ይህ ነውና።


በዚያም ወራት መጥምቁ ዮሐንስ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” ብሎ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ።


ካህ​ና​ቱም ያነ​ጹት ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ውስጥ ገቡ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መቅ​ደስ ያገ​ኙ​ትን ርኩስ ነገር ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ አወ​ጡት። ሌዋ​ው​ያ​ንም ወስ​ደው ወደ ሜዳ ወደ ቄድ​ሮን ወንዝ ጣሉት።


የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ ጣዖ​ታ​ትን ስለ ሠራች እና​ቱን ሐናን እቴጌ እን​ዳ​ት​ሆን ሻራት፤ አሳም የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዱን አስ​ቈ​ረ​ጠው፥ በቄ​ድ​ሮ​ንም ፈፋ አጠ​ገብ በእ​ሳት አቃ​ጠ​ለው።


ንጉ​ሡም ኤቲን፥ “ና ከእኔ ጋር ተሻ​ገር” አለው፤ ጌታ​ዊው ኤቲና ንጉ​ሡም፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ሕዝቡ ሁሉ ተሻ​ገሩ።


እዩ፤ እኔም እነሆ፥ ከእ​ና​ንተ ዘንድ ወሬ እስ​ኪ​መ​ጣ​ልኝ ድረስ በም​ድረ በዳው ውስጥ በሜ​ዳው እቈ​ያ​ለሁ” አለው።


የአ​ስ​ሬ​ሞ​ትም ሸለቆ ሁሉ እስከ ቄድ​ሮን ወንዝ ድረስ በም​ሥ​ራቅ በኩል እስ​ካ​ለው እስከ ፈረስ በር ማዕ​ዘን ድረስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ይሆ​ናል፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ነ​ቀ​ልም፤ አይ​ፈ​ር​ስ​ምም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች