Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 15:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 የመ​ጣ​ኸው ትና​ንት ነው፤ ዛሬ ከእኛ ጋር ላዙ​ር​ህን? እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በት እሄ​ዳ​ለሁ፤ አንተ ግን ተመ​ለስ፤ ወን​ድ​ሞ​ች​ህ​ንም ከአ​ንተ ጋር መል​ሳ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምሕ​ረ​ቱ​ንና እው​ነ​ቱን ያድ​ር​ግ​ልህ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 የመጣኸውም ገና ትናንት ነው፤ ታዲያ የት እንደምሄድ የማላውቅ ሰው እንዴት ዛሬ ከእኛ ጋራ እንድትንከራተት ላድርግ? በል አሁንም ሰዎችህን ይዘህ ተመለስ፤ በጎነትና ታማኝነትም ከአንተ ጋራ ይሁን” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 የመጣኸውም ገና ትናንት ነው፤ ታዲያ የት እንደምሄድ የማላውቅ ሰው እንዴት ዛሬ ከእኛ ጋር እንድትንከራተት ላድርግ? ተነሥ ሰዎችህን ይዘህ ተመለስ፤ ታማኝነትና እውነተኛነትም ከአንተ ጋር ይሁን” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 በዚህ አገር የኖርከውም ለአጭር ጊዜ ነው፤ ታዲያ አንተ ከእኔ ጋር የምትንከራተተው ስለምንድን ነው? እኔ የት እንደምሄድ እንኳ አላውቅም፤ ስለዚህ የአገርህን ሰዎች ይዘህ ተመለስ፤ እግዚአብሔር ቸርነቱንና እውነተኛነቱን ይግለጥልህ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 የመጣኸው ትናንት ነው፥ ዛሬ ከእኛ ጋር ላዙርህን? እኔ ወደምሄድበት እሄዳለሁ፥ አንተ ግን ተመለስ፥ ወንድሞችህንም ከአንተ ጋር ውሰድ፥ እግዚአብሔርም ምሕረቱንና እውነቱን ያድርግልህ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 15:20
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትና ስድ​ስት መቶ የሚ​ሆኑ ሰዎ​ችም ተነ​ሥ​ተው ከቂ​አላ ወጡ፤ ወደ​ሚ​ሄ​ድ​በ​ትም ይከ​ተ​ሉት ነበር። ሳኦ​ልም ዳዊት ከቂ​አላ እንደ ሸሸ ሰማ፤ ስለ​ዚ​ህም ከመ​ው​ጣት ቀረ።


አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሕ​ረ​ት​ንና ጽድ​ቅን ያድ​ር​ግ​ላ​ችሁ፤ ይህ​ንም ነገር አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና እኔ ደግሞ ይህን በጎ​ነት እመ​ል​ስ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


ኦሪት በሙሴ ተሰ​ጥ​ታን ነበ​ርና፤ ጸጋና እው​ነት ግን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሆነ​ልን።


ከባ​ሕ​ርም እስከ ባሕር ድረስ፥ ከሰ​ሜ​ንም እስከ ምሥ​ራቅ ድረስ ይቅ​በ​ዘ​በ​ዛሉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ለመ​ሻት ይር​ዋ​ር​ዋ​ጣሉ፤ አያ​ገ​ኙ​ት​ምም።


ስሕተተኞች ክፉን ያስባሉ፤ ደጋጎች ግን ምሕረትንና እውነትን ያስባሉ። ክፋትንም የሚሠሩ ምሕረትንና ይቅርታን አያውቁም። ነገር ግን ታማኝነትና ቸርነት ደግ በሚሠሩ ዘንድ ናቸው።


በማ​ለዳ ምሕ​ረ​ት​ህን እን​ጠ​ግ​ባ​ለ​ንና፤ በዘ​መ​ና​ችን ሁሉ ደስ ይለ​ናል፥ ሐሤ​ትም እና​ደ​ር​ጋ​ለን።


አቤቱ፥ ድን​ቅን የም​ታ​ደ​ርግ አንተ ታላቅ ነህና፥ አን​ተም ብቻ​ህን ታላቅ አም​ላክ ነህና፥


መድ​ኃ​ኒቴ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ክብ​ሬም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፥ የረ​ድ​ኤቴ አም​ላክ፥ ተስ​ፋ​ዬም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።


ኀጥ​ኣን ከማ​ኅ​ፀን ጀም​ረው ተለዩ፤ ከሆ​ድም ጀም​ረው ሳቱ፥ ሐሰ​ት​ንም ተና​ገሩ።


ክብሬ ይነሣ፥ በበ​ገ​ናና በመ​ሰ​ንቆ ይነሣ፤ እኔም ማልጄ እነ​ሣ​ለሁ።


በእ​ጃ​ቸው ተን​ኮል አለ​ባ​ቸው፥ ቀኛ​ቸ​ውም መማ​ለ​ጃን ተሞ​ል​ታ​ለች።


ምጽዋትና ሃይማኖት ከአንተ አይራቁ፤ በአንገትህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላትም ጻፋቸው፤


ዳዊ​ትም ወደ ኢያ​ቢስ ገለ​ዓድ ገዦች መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ ዳዊ​ትም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለቀ​ባው ለጌ​ታ​ችሁ ለሳ​ኦል ይህን ቸር​ነት አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና፥ እር​ሱ​ንና ልጁን ዮና​ታ​ን​ንም ቀብ​ራ​ች​ኋ​ቸ​ዋ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ባ​ረ​ካ​ችሁ ሁኑ።


የአ​ሕ​ዛብ ማኅ​በር ሁላ​ችሁ፥ በእ​ርሱ ታመኑ፥ ልባ​ች​ሁ​ንም በፊቱ አፍ​ስሱ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳ​ታ​ችን ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች