Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 15:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ንጉ​ሡም ጌታ​ዊ​ውን ኤቲን፥ “ከእኛ ጋር ለምን መጣህ? አንተ ከስ​ፍ​ራህ የመ​ጣህ ስደ​ተ​ኛና እን​ግዳ ነህና ተመ​ለስ፤ ከን​ጉ​ሡም ጋር ተቀ​መጥ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ንጉሡም ጋታዊውን ኢታይን እንዲህ አለው፤ “ከእኛ ጋራ የመጣኸው ለምንድን ነው? ተመለስና ከንጉሡ ከአቤሴሎም ጋራ ተቀመጥ፤ አንተ ለራስህ ከአገርህ ተወስደህ የመጣህ እንግዳ ነህ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ንጉሡም የጌታዊውን ሰው ኢታይን እንዲህ አለው፤ “አንተም ከእኛ ጋር አብረህ የመጣኸው ለምንድን ነው? ተመለስና ከንጉሥ አቤሴሎም ጋር ተቀመጥ፤ አንተ እኮ ከስፍራህ በግዞት የመጣህ መጻተኛ ነህ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ንጉሡም ኢታይ ተብሎ የሚጠራውን የጌት ሰው እንዲህ አለው፤ “ከእኛ ጋር ለምን ትሄዳለህ? ተመልሰህ ከአዲሱ ንጉሥ ጋር ቈይ፤ አንተ ከአገርህ ወጥተህ በመጻተኛነት እዚህ የምትኖር የውጪ አገር ሰው ነህ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ንጉሡም የጌት ሰው ኢታይን፦ ከእኛ ጋር ለምን መጣህ? አንተ ከስፍራህ የመጣህ እንግዳና ስደተኛ ነህና ተመለስ፥ ከንጉሡም ጋር ተቀመጥ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 15:19
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የመ​ጣ​ኸው ትና​ንት ነው፤ ዛሬ ከእኛ ጋር ላዙ​ር​ህን? እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በት እሄ​ዳ​ለሁ፤ አንተ ግን ተመ​ለስ፤ ወን​ድ​ሞ​ች​ህ​ንም ከአ​ንተ ጋር መል​ሳ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምሕ​ረ​ቱ​ንና እው​ነ​ቱን ያድ​ር​ግ​ልህ” አለው።


ዳዊ​ትም ሕዝ​ቡን ከኢ​ዮ​አብ እጅ በታች ሢሶ​ውን፥ ከኢ​ዮ​አ​ብም ወን​ድም ከሶ​ር​ህያ ልጅ ከአ​ቢሳ እጅ በታች ሢሶ​ውን፥ ከጌት ሰውም ከኤቲ እጅ በታች ሢሶ​ውን ላከ። ዳዊ​ትም ሕዝ​ቡን፥ “እኔ ደግሞ ከእ​ና​ንተ ጋር እወ​ጣ​ለሁ” አላ​ቸው።


ኑኃሚንም፦ እነሆ፥ ባልንጀራሽ ወደ ሕዝብዋና ወደ አማልክትዋ ተመልሳለች፣ አንቺም ደግሞ ከባልንጀራሽ ጋር ተመለሽ አለቻት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች