2 ሳሙኤል 15:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 አቤሴሎምም፥ “የመለከት ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ፥ አቤሴሎም በኬብሮን ነገሠ” በሉ የሚሉ ጕበኞችን ወደ እስራኤል ነገድ ሁሉ ላከ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ከዚያም አቤሴሎም፣ “የቀንደ መለከት ድምፅ ስትሰሙ፣ ‘አቤሴሎም በኬብሮን ነገሠ በሉ’ ” የሚሉ የምስጢር ሠራተኞችን በመላው የእስራኤል ነገዶች አሰማራ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ነገር ግን አቤሴሎም፥ በመላው የእስራኤል ነገዶች መሀል “የቀንደ መለከት ድምፅ ስትሰሙ፥ ‘አቤሴሎም በኬብሮን ነገሠ በሉ’ ” የሚሉ የምስጢር መልእክተኞችን ላከ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 “ነገር ግን ወደ እስራኤል ነገዶች ሁሉ መልእክተኞችን ልኮ የእምቢልታ ድምፅ በምትሰሙበት ጊዜ ድምፃችሁን ከፍ በማድረግ ‘አቤሴሎም የኬብሮን ንጉሥ ሆኗል!’ ብላችሁ ጩኹ” ብለው እንዲነግሩአቸው አደረገ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 አቤሴሎምም በእስራኤል ነገድ ሁሉ፦ የቀንደ መለከት ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ፦ አቤሴሎም በኬብሮን ነገሠ በሉ የሚሉ ጉበኞች ላከ። ምዕራፉን ተመልከት |