Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 14:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ለእ​ኔም ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ ሁለት ወን​ዶች ልጆች ነበ​ሩኝ፤ በሜ​ዳም ተጣሉ፤ የሚ​ገ​ላ​ግ​ላ​ቸ​ውም አል​ነ​በ​ረም፤ አን​ዱም ሌላ​ውን መትቶ ገደ​ለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እኔ አገልጋይህ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፤ ሜዳ ላይ እርስ በርሳቸው ተጣሉ፤ ገላጋይም ስላልነበረ፣ አንዱ ሌላውን መትቶ ገደለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እኔ አገልጋይህ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፤ ሜዳ ላይ እርስ በርሳቸው ተጣሉ፤ ገላጋይም ስላልነበረ፥ አንዱ ሌላውን መትቶ ገደለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ንጉሥ ሆይ! እኔ አገልጋይህ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፤ አንድ ቀን ገላጋይ በሌለበት ስፍራ ሁለቱ ልጆቼ እርስ በርሳቸው ተጣሉ፤ አንዱ ሌላውን ገደለው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ለእኔም ለባሪያህ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፥ በሜዳም ተጣሉ፥ የሚገላግላቸውም አልነበረም፥ አንዱም ሌላውን መትቶ ገደለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 14:6
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቃየ​ልም ወን​ድ​ሙን አቤ​ልን፥ “ና ወደ ሜዳ እን​ሂድ” አለው። በሜ​ዳም ሳሉ ቃየል በወ​ን​ድሙ በአ​ቤል ላይ ተነ​ሣ​በት፤ ገደ​ለ​ውም።


አቤ​ሴ​ሎ​ምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደ​ረገ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ “አም​ኖን የወ​ይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አም​ኖ​ንን ግደሉ ባል​ኋ​ችሁ ጊዜ ግደ​ሉት። አት​ፍ​ሩም፤ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁም እኔ ነኝና በርቱ፤ ጽኑም” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።


የአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምም አገ​ል​ጋ​ዮች አቤ​ሴ​ሎም እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው በአ​ም​ኖን ላይ አደ​ረ​ጉ​በት። የን​ጉ​ሡም ልጆች ሁሉ ተነ​ሥ​ተው በየ​በ​ቅ​ሎ​ዎ​ቻ​ቸው ተቀ​ም​ጠው ሸሹ።


ንጉ​ሡም፥ “ምን ሆነ​ሻል?” አላት። እር​ስ​ዋም አለች፥ “በእ​ው​ነት እኔ ባሌ የሞ​ተ​ብኝ ባል​ቴት ሴት ነኝ።


እነ​ሆም፥ ዘመ​ዶች ሁሉ በባ​ሪ​ያህ ላይ ተነሡ፤ ስለ ገደ​ለው ስለ ወን​ድሙ ነፍስ እን​ገ​ድ​ለው ዘንድ ወን​ድ​ሙን የገ​ደ​ለ​ውን አውጪ አሉኝ፤ እን​ዲ​ሁም ደግሞ ለባሌ ስምና ዘር በም​ድር ላይ እን​ዳ​ይ​ቀር ወራ​ሹን የቀ​ረ​ውን መብ​ራ​ቴን ያጠ​ፋሉ፤”


በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን ወጣ፤ ሁለ​ቱም የዕ​ብ​ራ​ው​ያን ሰዎች ሲጣሉ አየ፤ ሙሴም በዳ​ዩን፥ “ለምን ባል​ን​ጀ​ራ​ህን ትመ​ታ​ዋ​ለህ?” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች