Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 14:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ያችም ሴት አለች፥ “መል​ካ​ሙ​ንና ክፉ​ውን ነገር ለመ​ስ​ማት ንጉሡ ጌታዬ እንደ መሥ​ዋ​ዕ​ትና እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ነውና የጌ​ታዬ የን​ጉሡ ቃል እን​ደ​ዚሁ ነው፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ይሁን።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “አሁንም አገልጋይህ፤ ‘ንጉሥ ጌታዬ በጎውንና ክፉውን በመለየት እንደ እግዚአብሔር መልአክ ስለ ሆነ፣ የጌታዬ የንጉሡ ቃል ያጽናናኝ፤ እግዚአብሔር አምላክህም ካንተው ጋራ ይሁን’ ትላለች።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 አሁንም አገልጋይህ፤ ‘ንጉሥ ጌታዬ በጎውንና ክፉውን በመለየት እንደ እግዚአብሔር መልአክ ስለሆነ፥ የጌታዬ የንጉሡ ቃል ያጽናናኝ፤ ጌታ እግዚአብሔርም ከአንተው ጋር ይሁን’ ትላለች።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እንዲሁም ንጉሥ ሆይ! ንጉሥ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ስለ ሆነና መልካሙን ከክፉው ለይቶ ስለሚያውቅ የተስፋ ቃልህ በሰላም እንድኖር ይረዳኛል ብዬ አስቤ ነው እንግዲህ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን!”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እኔም ባሪያህ፦ መልካሙንና ክፉውን ነገር ለመስማት ንጉሡ ጌታዬ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነውና የጌታዬ የንጉሡ ቃል ያጽናናኛል፥ አምላክህም እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን አልሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 14:17
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉ​ሡም ለሴ​ቲቱ መልሶ፥ “የም​ጠ​ይ​ቅ​ሽን ነገር አት​ሰ​ው​ሪኝ” አላት። ሴቲ​ቱም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ይና​ገር” አለች።


ይህን ነገር እና​ገር ዘንድ እን​ድ​መጣ ይህን ምክር ያደ​ረገ አገ​ል​ጋ​ይህ ኢዮ​አብ ነው። ጌታዬ ግን በዚህ ዓለም የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ ታውቅ ዘንድ እንደ መል​አከ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ ጥበ​በኛ ነህ፤”


እር​ሱም በእኔ በባ​ሪ​ያህ ላይ ክፉ አደ​ረገ፤ አንተ ጌታዬ ንጉሥ ግን እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ነህ፤ በፊ​ት​ህም ደስ ያሰ​ኘ​ህን አድ​ርግ።


የአ​ባቴ ቤት ሁሉ በጌ​ታዬ በን​ጉሥ ዘንድ ሞት የሚ​ገ​ባ​ቸው ነበሩ፤ አንተ ግን እኔን ባሪ​ያ​ህን በገ​በ​ታህ በሚ​በሉ መካ​ከል አስ​ቀ​መ​ጥ​ኸኝ፤ ለን​ጉሥ ደግሞ ለመ​ና​ገር ምን መብት አለኝ?”


ንጉ​ሡም የፈ​ረ​ደ​ውን ፍርድ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ሰሙ፤ ፍር​ድን ለማ​ድ​ረግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ በእ​ርሱ ላይ እንደ ነበረ አይ​ተ​ዋ​ልና ከን​ጉሡ ፊት የተ​ነሣ ፈሩ።


ስለ​ዚ​ህም ሰምቶ በሕ​ዝ​ብህ ላይ መፍ​ረድ ይችል ዘንድ፥ መል​ካ​ሙ​ንና ክፉ​ው​ንም ይለይ ዘንድ ለባ​ሪ​ያህ አስ​ተ​ዋይ ልቡና ስጠው፤ አለ​ዚ​ያማ በዚህ በታ​ላቅ ሕዝብ ላይ ይፈ​ርድ ዘንድ ማን ይች​ላል?”


በአ​ን​ደ​በቴ በደል የለ​ምና አፌ ጕሮ​ሮ​ዬም ጥበ​ብን ይና​ገ​ራል።


ጠን​ካራ ምግብ ግን መል​ካ​ሙ​ንና ክፉ​ዉን ለመ​ለ​የት በሥ​ራ​ቸው የለ​መደ ልቡና ላላ​ቸው ለፍ​ጹ​ማን ሰዎች ነው።


በሁ​ሉም ለሙሴ እንደ ታዘ​ዝን እን​ዲሁ ለአ​ንተ ደግሞ እን​ታ​ዘ​ዛ​ለን፤ ብቻ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ ከአ​ንተ ጋር ይሁን።


አን​ኩ​ስም መልሶ ዳዊ​ትን፥ “በዐ​ይኔ ፊት ጻድቅ እንደ ሆንህ አው​ቃ​ለሁ፤ ነገር ግን የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች፦ ‘ከእኛ ጋር ወደ ሰልፍ አይ​ወ​ጣም’ አሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች