Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 13:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ምጣ​ዱ​ንም ወስዳ በፊቱ ገለ​በ​ጠች፤ እርሱ ግን ይበላ ዘንድ እንቢ አለ። አም​ኖ​ንም፥ “ሰውን ሁሉ ከእኔ ዘንድ አስ​ወጡ” አለ፤ ሰውም ሁሉ ከእ​ርሱ ዘንድ ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከዚያም መጋገሪያውን አውጥታ እንጀራውን አቀረበችለት፤ እርሱ ግን መብላት አልፈለገም። አምኖንም፣ “ሰውን ሁሉ ከዚህ አስወጡልኝ” አለ፤ ያለውም ሰው ሁሉ ትቶት ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ከዚያም መጋገሪያውን አውጥታ እንጀራውን አቀረበችለት፤ እርሱ ግን መብላት አልፈለገም። አምኖንም፥ “ሰውን ሁሉ ከዚህ አስወጡልኝ” አለ፤ ሰውም ሁሉ ትቶት ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የጋገረችውንም እንጀራ ከምጣዱ አውጥታ እንዲበላ አቀረበችለት፤ እርሱ ግን መመገቡን እምቢ ብሎ “ሰዎቹን ሁሉ አስወጡልኝ” አለ፤ ሁሉም ወጡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ምጣዱንም ወስዳ በፊቱ ገለበጠች እርሱ ግን ይበላ ዘንድ እንቢ አለ። አምኖንም፦ ሰውን ሁሉ ከእኔ ዘንድ አስወጡ አለ፥ ሰውም ሁሉ ከእርሱ ዘንድ ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 13:9
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዮሴ​ፍም በፊቱ ሰዎች ሁሉ ቆመው ሳሉ ሊታ​ገሥ አል​ተ​ቻ​ለ​ውም፥ “ሰዎ​ቹ​ንም ሁሉ ከፊቴ አስ​ወ​ጡ​ልኝ” ብሎ ተና​ገረ፤ ዮሴፍ ለወ​ን​ድ​ሞቹ ራሱን በገ​ለጠ ጊዜ በእ​ርሱ ዘንድ የቆመ ማንም አል​ነ​በ​ረም።


አም​ኖ​ንም ትዕ​ማ​ርን፥ “በእ​ጅሽ እበላ ዘንድ መብ​ሉን ወደ እል​ፍኙ አግ​ቢው” አላት፤ ትዕ​ማ​ርም የሠ​ራ​ች​ውን እን​ጎቻ ወስዳ ወን​ድ​ምዋ አም​ኖን ወዳ​ለ​በት እል​ፍኝ አገ​ባ​ችው።


ትዕ​ማ​ርም ወደ ወን​ድ​ምዋ ወደ አም​ኖን ቤት ሄደች፤ ተኝ​ቶም ነበር፤ ዱቄ​ትም ወስዳ ለወ​ሰች፤ በፊ​ቱም እን​ጎቻ አደ​ረ​ገች፤ ጋገ​ረ​ችም።


ሥራው ክፉ የሆነ ሁሉ ብር​ሃ​ንን ይጠ​ላ​ልና፤ ክፉም ስለ​ሆነ ሥራው እን​ዳ​ይ​ገ​ለ​ጥ​በት ወደ ብር​ሃን አይ​መ​ጣም።


ዔግ​ሎ​ምም ከገ​ል​ገል ከጣ​ዖ​ታቱ ቤት ተመ​ለሰ። ናዖ​ድም፥ “ንጉሥ ሆይ፥ ለብ​ቻህ የም​ነ​ግ​ርህ የም​ሥ​ጢር ነገር አለኝ” አለ፤ ዔግ​ሎ​ምም ሁሉ ከእ​ርሱ ዘንድ እን​ዲ​ወጣ አዘዘ፤ በእ​ር​ሱም ዘንድ የቆ​ሙት ሁሉ ወጡ ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች