Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 13:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 አቤ​ሴ​ሎም ግን ኰብ​ልሎ ወደ መአክ ሀገር ወደ ጌድ​ሶር ንጉሥ ወደ አሚ​ሁድ ልጅ ወደ ቶል​ማ​ይዮ ሄደ። ዳዊ​ትም ሁል ጊዜ ለልጁ ያለ​ቅስ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 አቤሴሎም ኰብልሎ የጌሹር ንጉሥ ወደ ሆነው ወደ ዓሚሁድ ልጅ ወደ ተልማይ ሄደ፤ ነገር ግን ዳዊት ስለ ሞተው ልጁ ዘወትር ያለቅስ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 አቤሴሎም ግን ኰብልሎ የገሹር ንጉሥ ወደ ሆነው ወደ ዓሚሁድ ልጅ ወደ ታልማይ ሄደ፤ ዳዊትም ዘወትር ስለ ልጁ ያለቅስ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37-38 አቤሴሎምም ሸሽቶ የገሹር ንጉሥ ወደ ሆነው ወደ ዓሚሁድ ልጅ ወደ ታልማይ ሄደ፤ በዚያም ሦስት ዓመት ቈየ፤ ዳዊት ስለ ልጁ ስለ አምኖን ሞት ለረዥም ጊዜ በማዘን አለቀሰ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 አቤሴሎም ግን ኮብልሎ ወደ ጌሹር ንጉሥ ወደ ዓሚሁድ ልጅ ወደ ተልማይ ሄደ። ዳዊትም ሁልጊዜ ለልጁ ያለቅስ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 13:37
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤ​ሴ​ሎ​ምም ኰበ​ለለ። ጕበ​ኛ​ውም ጐል​ማሳ ዐይ​ኑን ከፍ አደ​ረገ፤ እነ​ሆም፥ ብዙ ሰዎች በኋ​ላው በተ​ራ​ራው አጠ​ገብ በመ​ን​ገድ ሲመጡ አየ። ጕበ​ኛ​ውም መጥቶ ለን​ጉሡ እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “ብዙ ሰዎች በተ​ራ​ራው ጎን ባለው በአ​ር​ኖን መን​ገድ ሲመጡ አየሁ።”


ተና​ግ​ሮም በጨ​ረሰ ጊዜ እነሆ፥ ወዲ​ያው የን​ጉሥ ልጆች ገቡ፤ ድም​ፃ​ቸ​ው​ንም ከፍ አድ​ር​ገው አለ​ቀሱ፤ ደግ​ሞም ንጉ​ሡና ብላ​ቴ​ኖቹ ሁሉ እጅግ ታላቅ ልቅሶ አለ​ቀሱ።


ሴቲ​ቱም አለች፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ላይ እን​ዲህ ያለ ነገር ስለ​ምን አሰ​ብህ? ወይስ ንጉሥ ያሳ​ደ​ደ​ውን ስላ​ላ​ስ​መ​ለሰ እንደ በደል ከን​ጉሥ አፍ ይህ ቃል ወጥ​ቶ​አ​ልን?


ኢዮ​አ​ብም ተነ​ሥቶ ወደ ጌድ​ሶር ሄደ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ም​ንም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አመ​ጣው።


አቤ​ሴ​ሎ​ምም ኢዮ​አ​ብን፥ “ከጌ​ድ​ሶር ለምን መጣሁ? በዚ​ያም ተቀ​ምጬ ቢሆን ይሻ​ለኝ ነበር ብለህ እን​ድ​ት​ነ​ግ​ረው ወደ ንጉሥ እል​ክህ ዘንድ ወደ እኔ ና ብዬ ወደ አንተ ላክሁ፤ አሁ​ንም የን​ጉ​ሡን ፊት አላ​የ​ሁም፤ ኀጢ​አት ቢኖ​ር​ብኝ ይግ​ደ​ለኝ” አለው።


እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ በሶ​ርያ ጌድ​ሶር ሳለሁ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ቢመ​ል​ሰኝ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ር​ባ​ለሁ ብዬ ስእ​ለት ተስዬ ነበ​ርና” አለው።


ሁለ​ተ​ኛ​ውም ከቀ​ር​ሜ​ሎ​ሳ​ዊቱ ከአ​ቤ​ግያ የተ​ወ​ለ​ደው ዶሎ​ሕያ ነበረ። ሦስ​ተ​ኛ​ውም ከጌ​ድ​ሶር ንጉሥ ከቶ​ል​ሜ​ልም ልጅ ከመ​ዓክ የተ​ወ​ለ​ደው አቤ​ሴ​ሎም ነበረ።


ሦስ​ተ​ኛው አቤ​ሴ​ሎም ከጌ​ድ​ሶር ንጉሥ ከተ​ል​ማይ ልጅ ከመ​ዓካ፥ አራ​ተ​ኛው አዶ​ን​ያስ ከአ​ጊት፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች