Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 13:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ንጉ​ሡም ተነ​ሥቶ ልብ​ሱን ቀደደ፤ በም​ድር ላይም ወደቀ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ቁመው የነ​በሩ ብላ​ቴ​ኖቹ ሁሉ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀደዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ንጉሡም ተነሥቶ ቆመ፤ ልብሱን ቀደደ፤ በመሬትም ላይ ተዘረረ፤ በአጠገቡ ቆመው የነበሩት አገልጋዮቹም ሁሉ ልብሳቸውን ቀደዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ንጉሡም ከተቀመጠበት ተነሥቶ ልብሱን ቀደደ፤ በመሬትም ላይ ተዘረረ፤ በአጠገቡ ቆመው የነበሩት አገልጋዮቹም ሁሉ ልብሳቸውን ቀደዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ንጉሡ ከተቀመጠበት በመነሣት በሐዘን ልብሱን ቀዶ በመሬት ላይ ተዘረረ፤ በዚያ ከእርሱ ጋር የነበሩ አገልጋዮቹም በሐዘን ልብሳቸውን ቀደው በአጠገቡ በአክብሮት ቆሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ንጉሡም ተነሥቶ ልብሱን ቀደደ፥ በምድር ላይም ወደቀ፥ ባሪያዎቹም ሁሉ ልብሳቸውን ቀድደው በአጠገቡ ቆሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 13:31
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትም ስለ ሕፃኑ እግ​ዚ​አ​ሔ​ርን ለመነ፤ ዳዊ​ትም ጾመ፤ ገብ​ቶም በመ​ሬት ላይ ተኛ።


ዳዊ​ትም ልብ​ሱን ቀደደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ሰዎች ሁሉ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀደዱ።


ኢዮ​ብም ተነሣ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ው​ንም ቀደደ፥ ራሱ​ንም ተላጨ፥ በም​ድ​ርም ላይ ተደ​ፍቶ ሰገደ፤


ዳዊ​ትም ኢዮ​አ​ብ​ንና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ሁሉ፥ “ልብ​ሳ​ች​ሁን ቅደዱ፤ ማቅም ልበሱ፤ በአ​በ​ኔ​ርም ፊት አል​ቅሱ” አላ​ቸው። ንጉ​ሡም ዳዊት ከቃ​ሬ​ዛው በኋላ ሄደ።


ኢያ​ሱም ልብ​ሱን ቀደደ፤ እር​ሱና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት እስከ ማታ ድረስ በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ተደፉ፤ በራ​ሳ​ቸ​ውም ላይ ትቢያ ነሰ​ነሱ።


ያዕ​ቆ​ብም ልብ​ሱን ቀደደ፤ በወ​ገ​ቡም ማቅ ታጥቆ ለልጁ ብዙ ቀን አለ​ቀሰ።


ሮቤ​ልም ወደ ጕድ​ጓዱ ተመ​ለሰ፤ እነ​ሆም፥ ዮሴ​ፍን ከጕ​ድ​ጓድ በአ​ጣው ጊዜ ልብ​ሱን ቀደደ።


ገናም በመ​ን​ገድ ሲሄዱ ለዳ​ዊት፥ “አቤ​ሴ​ሎም የን​ጉ​ሡን ልጆች ሁሉ ገደ​ላ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ አል​ቀ​ረም” የሚል ወሬ መጣ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች