Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 12:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 የን​ጉ​ሣ​ቸ​ው​ንም የሜ​ል​ኮ​ምን ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ። ክብ​ደ​ቱም አንድ መክ​ሊት ወርቅ ያህል ነበር፤ ክቡር ዕን​ቍም ነበ​ረ​በት፤ ዳዊ​ትም በራሱ ላይ አደ​ረ​ገው። ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም እጅግ ብዙ ምርኮ አወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 የንጉሣቸውንም ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ፤ የዘውዱ ክብደት አንድ መክሊት ወርቅ የሚመዝን ሲሆን፣ በከበረ ዕንቍም ያጌጠ ነበር፤ ይህም በዳዊት ራስ ላይ ተጫነ። ዳዊትም ከከተማዪቱ እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰደ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 የንጉሣቸውንም ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ፤ የዘውዱ ክብደት የሚመዝነው አንድ መክሊት ወርቅ ሲሆን፥ በከበረ ዕንቁም ያጌጠ ነበር፤ ይህም በዳዊት ራስ ላይ ተጫነ። ዳዊትም ከከተማዪቱ እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰደ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ዳዊት የዐሞናውያን አምላክ ከሆነው ሚልኮም ተብሎ ከሚጠራው ጣዖት ራስ ላይ ሠላሳ አምስት ኪሎ ግራም የሚመዝነውንና በውስጡም የከበረ ዕንቊ ያለበትን ዘውድ ወስዶ በራሱ ላይ ደፋው፤ እንዲሁም ከከተማይቱ ብዙ ምርኮ ወሰደ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 የንጉሣቸውንም ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ። ክብደቱም አንድ መክሊት ወርቅ ያህል ነበር፥ ክቡር ዕንቁም ነበረበት፥ ዳዊትም በራሱ ላይ አደረገው። ከከተማይቱም እጅግ ብዙ ምርኮ አወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 12:30
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትም ሕዝ​ቡን ሁሉ ሰብ​ስቦ ወደ ራባት ሄደ፤ ወግ​ቶም ያዛት።


ዳዊ​ትም የን​ጉ​ሣ​ቸ​ውን የሞ​ል​ኮ​ልን ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ፤ ክብ​ደ​ቱም አንድ መክ​ሊት ወርቅ ያህል ሆኖ ተገኘ፤ ክቡር ዕን​ቍም ነበ​ረ​በት፤ በዳ​ዊ​ትም ራስ ላይ አስ​ቀ​መ​ጡት፤ ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰደ።


በእ​ስ​ራ​ኤል የተ​መ​ሰ​ገ​ንህ አንተ ግን በቅ​ዱ​ሳ​ንህ ትኖ​ራ​ለህ።


ብርንና ወርቅን ከእነርሱ ውሰድ፥ አክሊሎችንም ሥራ፣ በታላቁም ካህን በኢዮሴዴቅ ልጅ በኢያሱ ራስ ላይ ድፋቸው፥ እንዲህም በለው፦


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች