Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 12:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ዳዊ​ትም ሚስ​ቱን ቤር​ሳ​ቤ​ህን አጽ​ና​ናት፤ ወደ እር​ስ​ዋም ገባ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ተኛ፤ ፀነ​ሰ​ችም፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም ሰሎ​ሞን ብሎ ጠራው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ​ደው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ከዚያም ዳዊት ሚስቱን ቤርሳቤህን አጽናናት፤ ወደ እርሷም ገብቶ ዐብሯት ተኛ፤ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሰሎሞን አለው። እግዚአብሔርም ወደደው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ከዚያም ዳዊት ሚስቱን ቤርሳቤህን አጽናናት፤ ወደ እርሷም ገብቶ አብሮአት ተኛ፤ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሰሎሞን አለው። ጌታም ወደደው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ከዚህ በኋላ ዳዊት ሚስቱን ቤርሳቤህን አጽናናት፤ ከእርስዋም ጋር ግንኙነት አደረገ፤ እርስዋም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ዳዊትም የልጁን ስም “ሰሎሞን” ብሎ ጠራው፤ እግዚአብሔር ሕፃኑን ስለ ወደደው፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ዳዊትም ሚስቱን ቤርሳቤህን አጽናናት፥ ወደ እርስዋም ገባ፥ ከእርስዋም ጋር ተኛ፥ ወንድ ልጅም ወለደች፥ ስሙንም ሰሎሞን ብሎ ጠራው። እግዚአብሔርም ወደደው፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 12:24
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ፤ ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ።


ንጉሡ ዳዊ​ትም ለጉ​ባ​ኤው ሁሉ እን​ዲህ አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ​ውን የመ​ረ​ጠው ልጄ ሰሎ​ሞን ገና ለጋ ብላ​ቴና ነው፤ ሕን​ጻው ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ም​ላክ ነው እንጂ ለሰው አይ​ደ​ለ​ምና ሥራው ታላቅ ነው።


እነ​ዚህ ደግሞ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ ከዓ​ሚል ልጅ ከቤ​ር​ሳ​ቤህ ስማዕ፥ ሶባብ፥ ናታን፥ ሰሎ​ሞን፥ አራት፤


ዕድ​ሜ​ህም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፤ ከአ​ባ​ቶ​ች​ህም ጋር ባን​ቀ​ላ​ፋህ ጊዜ፥ ከወ​ገ​ብህ የሚ​ወ​ጣ​ውን ዘር​ህን ከአ​ንተ በኋላ አስ​ነ​ሣ​ለሁ፤ መን​ግ​ሥ​ቱ​ንም አዘ​ጋ​ጃ​ለሁ ።


ደግ​ሞም በነ​ቢዩ በና​ታን እጅ ልኮ ስሙን ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍቁረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብሎ ጠራው።


ነገር ግን ነቢ​ዩን ናታ​ንን፥ በና​ያ​ስ​ንም፥ ኀያ​ላ​ኑ​ንም፥ ወን​ድ​ሙ​ንም ሰሎ​ሞ​ንን አል​ጠ​ራም።


ናታ​ንም የሰ​ሎ​ሞ​ንን እናት ቤር​ሳ​ቤ​ህን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራት፥ “ጌታ​ችን ዳዊት ሳያ​ውቅ የአ​ጊት ልጅ አዶ​ን​ያስ እንደ ነገሠ አል​ሰ​ማ​ሽ​ምን?


የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሰሎ​ሞን በዚህ ነገር ኀጢ​አት አድ​ርጎ የለ​ምን? በብዙ አሕ​ዛ​ብም መካ​ከል እንደ እርሱ ያለ ንጉሥ አል​ነ​በ​ረም፤ በአ​ም​ላ​ኩም ዘንድ የተ​ወ​ደደ ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ አን​ግ​ሦት ነበር፤ እር​ሱ​ንም እንኳ እን​ግ​ዶች ሴቶች አሳ​ቱት።


ስለ ብን​ያ​ምም እን​ዲህ አለ፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ወ​ደደ በእ​ርሱ ዘንድ ተማ​ምኖ ይኖ​ራል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዘ​መኑ ሁሉ ይጋ​ር​ደ​ዋል፤ በት​ከ​ሻ​ውም መካ​ከል ያድ​ራል።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት ስማ​ቸው ይህ ነው፤ ሳሚስ፥ ሶባብ፥ ናታን፥ ሰሎ​ሞን፥


እኔም አባቴን የምሰማ ልጅ ነበርሁና፥ በእናቴም ፊት እወደድ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች