Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 12:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ሕፃኑ ሞተ። የዳ​ዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖች፥ “ሕፃኑ በሕ​ይ​ወት ሳለ ብን​ነ​ግ​ረው አል​ሰ​ማ​ንም፤ ይል​ቁ​ንስ ሕፃኑ እንደ ሞተ ብን​ነ​ግ​ረው እን​ዴት ይሆን? በራሱ ላይ ክፉ ያደ​ር​ጋል” ብለው ሕፃኑ እንደ ሞተ ይነ​ግ​ሩት ዘንድ ፈሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በሰባተኛው ቀን ሕፃኑ ሞተ፤ የዳዊት አገልጋዮችም፣ “እነሆ ሕፃኑ በሕይወት እያለ የነገርነውን ዳዊት አልሰማንም፤ ታዲያ አሁን የሕፃኑን መሞት እንዴት አድርገን ልንነግረው እንችላለን? በራሱ ላይ ጕዳት ሊያደርስ ይችላል” ብለው መንገሩን ፈሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በሰባተኛው ቀን ሕፃኑ ሞተ፤ የዳዊት አገልጋዮችም፥ “እነሆ ሕፃኑ በሕይወት እያለ የነገርነውን ዳዊት አልሰማንም ታዲያ አሁን የሕፃኑን መሞት እንዴት አድርገን ልንነግረው እንችላለን? በራሱ ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል” ብለው መንገሩን ፈሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ከአንድ ሳምንትም በኋላ ሕፃኑ ሞተ፤ የዳዊት ባለሟሎችም መርዶውን ለመንገር ፈርተው “ሕፃኑ በሕይወት በነበረበት ጊዜ እንኳ ዳዊት ስንመክረው አልሰማንም፤ ታዲያ፥ አሁን የልጁን መሞት እንዴት አድርገን ልንነግረው እንችላለን? ምናልባት በራሱ ላይ አንዳች ጒዳት ማድረስ ይችል ይሆናል!” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በሰባተኛውም ቀን ሕፃኑ ሞተ። የዳዊትም ባሪያዎች፦ ሕፃኑ በሕይወት ሳለ ብንነግረው አልሰማንም፥ ይልቁንስ ሕፃኑ እንደ ሞተ ብንነግረው እንዴት ይሆን? በነፍሱ ክፉ ያደርጋል ብለው ሕፃኑ እንደ ሞተ ይነግሩት ዘንድ ፈሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 12:18
3 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አባ​ቶ​ቻ​ችን ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በግ​ብ​ፅም እጅግ ዘመን ተቀ​መ​ጥን፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም እኛ​ንና አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን በደሉ።


የቤ​ቱም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ተነ​ሥ​ተው ከም​ድር ያነ​ሡት ዘንድ በአ​ጠ​ገቡ ቆሙ፤ እርሱ ግን እንቢ አለ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር እን​ጀራ አል​በ​ላም።


ዳዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖቹ በሹ​ክ​ሹ​ክታ ሲነ​ጋ​ገሩ ባየ ጊዜ ዳዊት ሕፃኑ እንደ ሞተ ዐወቀ፤ ዳዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “ሕፃኑ ሞቶ​አል?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “ሞቶ​አል” አሉት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች