Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 12:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ናታ​ንም ወደ ቤቱ ተመ​ለሰ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የኦ​ርዮ ሚስት ለዳ​ዊት የወ​ለ​ደ​ች​ውን ሕፃን ቀሠ​ፈው፤ እጅ​ግም ታምሞ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ናታን ወደ ቤቱ ከሄደ በኋላ፣ የኦርዮ ሚስት ለዳዊት የወለደችለትን ሕፃን እግዚአብሔር ከባድ ሕመም ላይ ጣለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ናታን ወደ ቤቱ ከሄደ በኋላ፥ የኦርዮን ሚስት ለዳዊት የወለደችለትን ሕፃን ጌታ ከባድ ሕመም ላይ ጣለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ከዚህ በኋላ ናታን ወደ ቤቱ ሄደ። የኦርዮ ሚስት ለዳዊት የወለደችለትን ልጅ እግዚአብሔር በከባድ ሕመም ቀሠፈው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ናታንም ወደ ቤቱ ተመለሰ። እግዚአብሔርም የኦርዮ ሚስት ለዳዊት የወለደችውን ሕፃን ቀሠፈ፥ እጅግም ታምሞ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 12:15
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዐ​ሥር ቀንም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ናባ​ልን ቀሠ​ፈው፤ እር​ሱም ሞተ።


ውኃ​ቸ​ውን ደም አደ​ረገ፥ ዓሦ​ቻ​ቸ​ው​ንም ገደለ።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ስለ አል​ሰጠ ያን​ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ቀሠ​ፈው፤ ተል​ቶም ሞተ።


ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ከዚያ በኋላ በአ​ብያ ዘመን አል​በ​ረ​ታም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀሠ​ፈው፤ ሞተም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ንጉ​ሡን በደዌ ዳሰ​ሰው፤ እስ​ከ​ሚ​ሞ​ት​በ​ትም ቀን ለም​ጻም ሆነ፤ በተ​ለየ ቤትም ይቀ​መጥ ነበር፤ የን​ጉ​ሡም ልጅ ኢዮ​አ​ታም በን​ጉሡ ቤት ላይ ሠል​ጥኖ ለሀ​ገሩ ሕዝብ ይፈ​ርድ ነበር።


ደግ​ሞም ዳዊት አለው፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካል​ገ​ደ​ለው፥ ወይም ቀኑ ደርሶ ካል​ሞተ፥ ወይም ወደ ጦር​ነት ወርዶ ካል​ሞተ እኔ አል​ገ​ድ​ለ​ውም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእ​ኔም በቀር አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ዕወቁ፤ ዕወቁ። እኔ እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ አድ​ን​ማ​ለሁ፤ እኔ እገ​ር​ፋ​ለሁ፤ ይቅ​ርም እላ​ለሁ፤ ከእ​ጄም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም።


ነገር ግን በዚህ ነገር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶች መነ​ሣ​ሣት ምክ​ን​ያት አድ​ር​ገ​ሃ​ልና ስለ​ዚህ ደግሞ የተ​ወ​ለ​ደ​ልህ ልጅ ፈጽሞ ይሞ​ታል” አለው።


ዳዊ​ትም ስለ ሕፃኑ እግ​ዚ​አ​ሔ​ርን ለመነ፤ ዳዊ​ትም ጾመ፤ ገብ​ቶም በመ​ሬት ላይ ተኛ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች