Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 10:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ሐኖ​ንም የዳ​ዊ​ትን አገ​ል​ጋ​ዮች ወስዶ የጢ​ማ​ቸ​ውን ገሚስ ላጨ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም እስከ ወገ​ባ​ቸው ድረስ ከሁ​ለት ቀድዶ ሰደ​ዳ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ስለዚህ ሐኖን የዳዊትን ሰዎች ይዞ፣ የእያንዳንዳቸውን ጢም በከፊል ላጨ፣ ልብሳቸውንም ወገባቸው ድረስ አሳጥሮ በመቍረጥ መልሶ ሰደዳቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ስለዚህ ሐኑን የዳዊትን አገልጋዮች ይዞ፥ የእያንዳንዳቸውን ጢም በከፊል ላጨ፥ ልብሳቸውንም ወገባቸው ድረስ አሳጥሮ በመቁረጥ መልሶ ሰደዳቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ሐኑን የዳዊትን መልእክተኞች ይዞ በአንድ በኩል ጺማቸውን ላጨ፤ ልብሳቸውንም በመቊረጥ እስከ ወገባቸው አሳጥሮ አባረራቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ሐኖንም የዳዊትን ባሪያዎች ወስዶ የጢማቸውን ገሚስ ላጨ፥ ልብሳቸውንም እስከ ወገባቸው ድረስ ከሁለት ቀድዶ ሰደዳቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 10:4
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለዳ​ዊ​ትም ስለ ሰዎቹ ነገ​ሩት፤ ሰዎቹ እጅግ አፍ​ረው ነበ​ሩና ተቀ​ባ​ዮ​ችን ላከ። ንጉ​ሡም፥ “ጢማ​ችሁ እስ​ኪ​ያ​ድግ ድረስ በኢ​ያ​ሪኮ ተቀ​መጡ፤ ከዚ​ያም በኋላ ተመ​ለሱ” አላ​ቸው።


ለራ​ሳ​ችሁ እዘኑ፤ ጣዖ​ታ​ች​ሁና መሠ​ዊ​ያ​ችሁ ያሉ​ባት ዲቦን ትጠ​ፋ​ለ​ችና፤ ወደ​ዚ​ያም ወጥ​ታ​ችሁ በሞ​ዓብ ናባው አል​ቅሱ፤ ወዮም በሉ፤ ራስ ሁሉ በራ ይሆ​ናል፤ ክን​ድም ሁሉ ይቈ​ረ​ጣል።


እን​ዲሁ የአ​ሦር ንጉሥ የግ​ብ​ፅ​ንና የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያን ምርኮ፥ ጐበ​ዛ​ዝ​ቱ​ንና ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹን ራቁ​ታ​ቸ​ው​ንና ባዶ እግ​ራ​ቸ​ውን አድ​ርጎ፥ ገላ​ቸ​ው​ንም ገልጦ ለግ​ብፅ ኀፍ​ረት ይነ​ዳ​ቸ​ዋል።


ጢማ​ቸ​ውን ላጭ​ተው፥ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ቀድ​ደው እያ​ለ​ቀሱ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ያቀ​ርቡ ዘንድ የእ​ህል ቍር​ባ​ንና ዕጣን በእ​ጃ​ቸው የያዙ፥ ሰማ​ንያ ሰዎች ከሴ​ኬ​ምና ከሴሎ፥ ከሰ​ማ​ር​ያም መጡ።


የራስ ጠጕ​ራ​ች​ሁ​ንም ዙሪ​ያ​ውን አት​ከ​ር​ክ​ሙት፤ ጢማ​ች​ሁ​ንም አት​ላጩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች