Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 1:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ሳኦ​ልና ዮና​ታን የተ​ወ​ደ​ዱና ያማሩ ነበሩ፤ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸ​ውና በሞ​ታ​ቸው አል​ተ​ለ​ያ​ዩም፤ ከን​ስር ይልቅ ፈጣ​ኖች ነበሩ፤ ከአ​ን​በ​ሳም ይልቅ ብር​ቱ​ዎች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ሳኦልና ዮናታን በሕይወት እያሉ፣ የሚዋደዱና የሚስማሙ ነበሩ፤ ሲሞቱም አልተለያዩም፤ ከንስርም ይልቅ ፈጣኖች፣ ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ሳኦልና ዮናታን፥ የተዋደዱና የተስማሙ፤ በሕይወትም ሆነ በሞት ያልተለያዩ፤ ከንስርም ይልቅ የፈጠኑ፥ ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 “ሳኦልና ዮናታን በአስደናቂ ፍቅር ኖሩ፤ በሕይወትም ሆነ በሞት ላለመለያየት ተባበሩ፤ እነርሱም ከንስር የፈጠኑ፥ ከአንበሳም የበረቱ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ሳኦልና ዮናታን የተዋደዱና የተስማሙ ነበሩ፥ በሕይወታቸውና በሞታቸው አልተለያዩም፥ ከንስር ይልቅ ፈጣኖች ነበሩ፥ ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 1:23
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆ! እንደ ደመና ይወ​ጣል፤ ሰረ​ገ​ሎ​ቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ናቸው፤ ፈረ​ሶ​ቹም ከን​ስር ይልቅ ፈጣ​ኖች ናቸው። ተዋ​ር​ደ​ና​ልና ወዮ​ልን።


በሰ​ባ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ቀን ፀሐይ ሳት​ገባ የከ​ተ​ማ​ዪቱ ሰዎች፥ “ከማር የሚ​ጣ​ፍጥ ምን​ድን ነው? ከአ​ን​በ​ሳስ የሚ​በ​ረታ ማን ነው?” አሉት። ሶም​ሶ​ንም፥ “በጥ​ጃዬ ባላ​ረ​ሳ​ችሁ ኑሮ የእ​ን​ቆ​ቅ​ል​ሼን ትር​ጓሜ ባላ​ወ​ቃ​ች​ሁም ነበር” አላ​ቸው።


ቆፍ። አሳ​ዳ​ጆ​ቻ​ችን ከሰ​ማይ ንስር ይልቅ ፈጣ​ኖች ሆኑ፤ በተ​ራ​ሮች ላይ አሳ​ደ​ዱን፤ በም​ድረ በዳም ሸመ​ቁ​ብን።


የመ​ር​ከብ መን​ገድ ፍለጋ፥ ወይም የሚ​በ​ርና የሚ​በ​ላ​ውን የሚ​ፈ​ልግ የን​ስር ፍለጋ እን​ደ​ማ​ይ​ታ​ወቅ ሕይ​ወቴ እን​ዲሁ ሆነ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊት ለሳ​ኦል መን​ገ​ሩን በፈ​ጸመ ጊዜ የዮ​ና​ታን ነፍስ በዳ​ዊት ነፍስ ታሰ​ረች፤ ዮና​ታ​ንም እንደ ነፍሱ ወደ​ደው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ንስር እን​ደ​ሚ​በ​ርር ከሩቅ ሀገር፥ ከም​ድር ዳር ቋን​ቋ​ቸ​ውን የማ​ት​ሰ​ማ​ውን ሕዝብ፥


ዳዊ​ትም በም​ድረ በዳ ውስጥ ባለ​ችው በአ​ን​ባ​ዪቱ ሳለ ከጋድ ወገን የሆኑ እነ​ዚህ ጋሻና ጦር የሚ​ይዙ፥ ጽኑ​ዓን፥ ኀያ​ላን ሰል​ፈ​ኞች፥ ወደ እርሱ ተጠጉ፤ ፊታ​ቸ​ውም እንደ አን​በሳ ፊት ነበረ፤ በተ​ራ​ራም ላይ እን​ደ​ሚ​ዘ​ልል ሚዳቋ ፈጣ​ኖች ነበሩ።


በቀ​በ​ስ​ሄል የነ​በ​ረው ታላቅ ሥራ ያደ​ረ​ገው የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ የሞ​ዓ​ባ​ዊ​ውን የአ​ር​ኤ​ልን ሁለት ልጆች ገደለ፤ በአ​መ​ዳ​ዩም ወራት ወርዶ በጕ​ድ​ጓድ ውስጥ አን​በሳ ገደለ።


ዮና​ታ​ንም፥ “ይህ​ንስ ያር​ቀው፤ አት​ሞ​ትም፤ እነሆ፥ አባቴ አስ​ቀ​ድሞ ለእኔ ሳይ​ገ​ልጥ ትል​ቅም ሆነ ትንሽ ነገር ቢሆን አያ​ደ​ር​ግም፤ አባ​ቴስ ይህን ነገር ለምን ይሰ​ው​ረ​ኛል? እን​ዲህ አይ​ደ​ለም” አለው።


በዚ​ያም ሦስቱ የሦ​ር​ህያ ልጆች ኢዮ​አ​ብና አቢሳ፥ አሣ​ሄ​ልም ነበሩ፤ የአ​ሣ​ሄ​ልም እግ​ሮቹ ፈጣ​ኖች ነበሩ፤ እንደ ዱር ሚዳ​ቋም ሯጭ ነበረ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ሴቶች ልጆች ሆይ፥ ቀይ ሐርና ጥሩ ግምጃ ያለ​ብ​ሳ​ችሁ ለነ​በረ፥ በወ​ር​ቀ​ዘ​ቦም ያስ​ጌ​ጣ​ችሁ ለነ​በረ ለሳ​ኦል አል​ቅ​ሱ​ለት።


ጕሮ​ሮው እጅግ ጣፋጭ ነው፥ ሁለ​ን​ተ​ና​ውም የተ​ወ​ደደ ነው፤ እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ ልጅ ወን​ድሜ ይህ ነው፥ ወዳ​ጄም ይህ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች