Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ጴጥሮስ 2:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ራሳቸው የጥፋት ባሪያዎች ሆነው “አርነት ትወጣላችሁ፤” እያሉ ተስፋ ይሰጡአቸዋል፤ ሰው ለተሸነፈበት ለእርሱ ተገዝቶ ባሪያ ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እነርሱ ራሳቸው የጥፋት ባሮች ሆነው ሳሉ፣ ሌሎችን ነጻ ትወጣላችሁ እያሉ ተስፋ ይሰጧቸዋል፤ ሰው ለተገዛለት ለዚያ ነገር ባሪያ ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ራሳቸው የጥፋት ባርያዎች ሆነው “ነጻ ትወጣላችሁ፤” እያሉ ተስፋ ይሰጧቸዋል፤ ሰው ለተሸነፈበት ለእርሱ የተገዛ ባርያ ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 “ነጻ ትወጣላችሁ” እያሉ ተስፋ ይሰጡአቸዋል። ሰው ሲሸነፍ ላሸናፊው ባሪያ ሆኖ ስለሚገዛ እነርሱም ራሳቸው የኃጢአት ባሪያዎች ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ራሳቸው የጥፋት ባሪያዎች ሆነው፦ አርነት ትወጣላችሁ እያሉ ተስፋ ይሰጡአቸዋል፤ ሰው ለተሸነፈበት ለእርሱ ተገዝቶ ባሪያ ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ጴጥሮስ 2:19
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ኀጢ​ኣ​ትን የሚ​ሠራ ሁሉ የኀ​ጢ​ኣት ባርያ ነው።


ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እና​ን​ተስ ለነ​ጻ​ነት ተጠ​ር​ታ​ች​ኋል፤ ነገር ግን በሥ​ጋ​ችሁ ፈቃድ ለነ​ጻ​ነ​ታ​ችሁ ምክ​ን​ያት አታ​ድ​ር​ጉ​ላት፤ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁም በፍ​ቅር ተገዙ።


አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ።


እን​ግ​ዲህ ጸን​ታ​ችሁ ቁሙ፤ እንደ ገናም በባ​ር​ነት ቀን​በር አት​ኑሩ።


እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።


ስለ ነቢ​ያት ልቤ በው​ስጤ ተሰ​ብ​ሮ​አል፤ አጥ​ን​ቶ​ችም ሁሉ ታው​ከ​ዋል፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የተ​ነሣ፤ ከጌ​ት​ነ​ቱም ክብር የተ​ነሣ እኔም በመ​ከራ እንደ ተቀ​ጠ​ቀጠ ሰው፥ የወ​ይን ጠጅ እን​ዳ​ሸ​ነ​ፈ​ውም እንደ ሰካ​ራም ሰው ሆኛ​ለሁ።


ለኤ​ፍ​ሬም ምን​ደ​ኞች ትዕ​ቢት አክ​ሊል፥ ያለ ወይን ጠጅ ለሰ​ከሩ፥ በወ​ፍ​ራም ተራራ ራስ ላይ ላለ​ችም ለረ​ገ​ፈች ለክ​ብር ጌጥ አበባ ወዮ!


በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዕውቀት ከዓለም ርኵሰት ካመለጡ በኋላ ዳግመኛ በእርስዋ ተጠላልፈው የተሸነፉ ቢሆኑ፥ ከፊተኛው ኑሮአቸው ይልቅ የኋለኛው የባሰ ሆኖባቸዋል።


ያም ክፉ መን​ፈስ የያ​ዘው ሰው ተነ​ሣ​ባ​ቸው፤ አየ​ለ​ባ​ቸ​ውም፤ አሸ​ነ​ፋ​ቸ​ውም፤ አቍ​ስ​ሎም ከዚያ ቤት አስ​ወ​ጥቶ አባ​ረ​ራ​ቸው።


ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ በተስፋው ቃል ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን።


ካህ​ኑም ያያል፤ እነ​ሆም፥ ምል​ክቱ በቆ​ዳው ላይ ቢሰፋ ካህኑ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለ​ዋል፤ ለምጽ ነውና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች