Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 9:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ኢዩም ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ሄደ፤ ኤል​ዛ​ቤ​ልም ይህን በሰ​ማች ጊዜ ዐይ​ን​ዋን ተኳ​ለች፤ ራስ​ዋ​ንም አስ​ጌ​ጠች፤ በመ​ስ​ኮ​ትም ዘልቃ ትመ​ለ​ከት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ከዚያም ኢዩ ወደ ኢይዝራኤል ሄደ፤ ኤልዛቤልም ይህን በሰማች ጊዜ ዐይኗን ተኳኵላ፣ ጠጕሯንም አሰማምራ በመስኮት ትመለከት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 በዚህም ጊዜ ኢዩ ወደ ኢይዝራኤል ደረሰ፤ ኤልዛቤልም ይህን የሆነውን ነገር ሰምታ ዐይንዋን ተኳለች፤ ጠጉርዋንም ተሠርታ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ላይ በመስኮት አዘንብላ ቁልቁል መንገዱን ትመለከት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 በዚህም ጊዜ ኢዩ ወደ ኢይዝራኤል ደረሰ፤ ኤልዛቤልም ይህን የሆነውን ነገር ሰምታ ዐይንዋን ተኳለች፤ ጠጒርዋንም ተሠርታ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ላይ በመስኮት አዘንብላ ቊልቊል መንገዱን ትመለከት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ኢዩም ወደ ኢይዝራኤል መጣ፤ ኤልዛቤልም በሰማች ጊዜ ዐይንዋን ተኳለች፤ ራስዋንም አስጌጠች፤ በመስኮትም ዘልቃ ትመለከት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 9:30
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አን​ቺስ ምን ታደ​ር​ጊ​ያ​ለሽ? ቀይ በለ​በ​ስሽ ጊዜ፥ በወ​ርቅ አን​ባ​ርም ባጌ​ጥሽ ጊዜ፥ ዐይ​ን​ሽ​ንም በኵል በተ​ኳ​ልሽ ጊዜ፥ በከ​ንቱ ታጌ​ጫ​ለሽ፤ ፍቅ​ረ​ኞ​ችሽ አቃ​ለ​ሉሽ፥ ነፍ​ስ​ሽን ይሹ​አ​ታል።


ከሩቅ ሀገ​ርም ወደ​መጡ ሰዎች መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላኩ፤ እነ​ር​ሱም በደ​ረሱ ጊዜ ይታ​ጠ​ባሉ፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይኳ​ላሉ፤ ያጌ​ጣ​ሉም።


በቀ​ስታ ተክዝ፤ ነገር ግን የሙ​ታ​ንን ልቅሶ አታ​ል​ቅስ፤ መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያ​ህን በራ​ስህ ላይ አድ​ርግ፤ ጫማ​ህ​ንም በእ​ግ​ርህ አጥ​ልቅ፤ ከን​ፈ​ሮ​ች​ህ​ንም አት​ሸ​ፍን፤ የዕ​ዝን እን​ጀ​ራ​ንም አት​ብላ።”


ለእናንተም ጠጕርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጎናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ፤


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ ወደ አፌቅ ሰበ​ሰቡ፤ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ባለው ውኃ ምንጭ አጠ​ገብ ሰፈሩ።


የእ​ኩ​ሌ​ቶቹ ፈረ​ሶች አለቃ ዘም​ሪም አሽ​ከ​ሮ​ቹን ሁሉ ሰብ​ስቦ ዐመፀ፤ ኤላም በቴ​ርሳ ነበረ፤ በቴ​ር​ሳም በነ​በ​ረው በመ​ጋ​ቢው በአሳ ቤት ይሰ​ክር ነበር።


የሶ​ር​ያም ንጉሥ አገ​ል​ጋ​ዮች እን​ዲህ አሉት፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የተ​ራ​ሮች አም​ላክ ነው እንጂ የሸ​ለቆ አም​ላክ አይ​ደ​ለም፤ ስለ​ዚህ በር​ት​ተ​ው​ብን ነበር፤ ነገር ግን በሜዳ ብን​ዋ​ጋ​ቸው ድል እና​ደ​ር​ጋ​ቸው ነበር።


ውበቷ ድል አይንሣህ። በዐይኖችዋ አትጠመድ፥ በቅንድቧም አትማረክ።


የምንዝር ጌጥ ያላት የጐልማሶችን ልብ እንዲሰቀል የምታደርግ ሴት ያንጊዜ ትገናኘዋለች። እርስዋ የምትበርር መዳራትንም የምትወድ ናት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች