Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 9:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ኢዮ​ራ​ምም፥ “ሰረ​ገላ አዘ​ጋጁ” አለ፤ ሰረ​ገ​ላ​ው​ንም አዘ​ጋ​ጁ​ለት። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ኢዮ​ራ​ምና የይ​ሁዳ ንጉሥ አካ​ዝ​ያስ ሁለ​ቱም በሰ​ረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸው ተቀ​ም​ጠው ወጡ፤ ኢዩ​ንም ሊገ​ና​ኙት ሄዱ፤ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊ​ውም በና​ቡቴ እርሻ ውስጥ አገ​ኙት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ኢዮራምም፣ “ሠረገላዬን አዘጋጁ” ብሎ አዘዘ። ሠረገላው እንደ ተዘጋጀም፣ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮራምና የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ በየሠረገሎቻቸው ሆነው ኢዩን ለመገናኘት ሄዱ፤ የኢይዝራኤላዊው የናቡቴ ርስት በነበረው ዕርሻ ላይም ተገናኙት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ኢዮራም “ሠረገላዬን አዘጋጅልኝ” ሲል ትእዛዝ ሰጠ፤ ሠረገላውም ተዘጋጅቶለት እርሱና ንጉሥ አካዝያስ በየግል ሠረገላቸው እየጋለቡ ኢዩን ሊገናኙት ወጡ፤ እነርሱም ኢዩን ቀድሞ የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ አገኙት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ኢዮራም “ሠረገላዬን አዘጋጅልኝ” ሲል ትእዛዝ ሰጠ፤ ሠረገላውም ተዘጋጅቶለት እርሱና ንጉሥ አካዝያስ በየግል ሠረገላቸው እየጋለቡ ኢዩን ሊገናኙት ወጡ፤ እነርሱም ኢዩን ቀድሞ የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ አገኙት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ኢዮራምም “ሠረገላ አዘጋጁ፤” አለ፤ ሠረገላውንም አዘጋጁለት። የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮራም የይሁዳም ንጉሥ አካዝያስ በሠረገሎቻቸው ተቀምጠው ወጡ፤ ኢዩንም ሊገናኙት ሄዱ፤ በኢይዝራኤላዊው በናቡቴ እርሻ ውስጥ አገኙት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 9:21
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወደ ኢዮ​ራም በመ​ም​ጣ​ቱም የአ​ካ​ዝ​ያስ ጥፋት ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆነ፤ በመ​ጣም ጊዜ ከኢ​ዮ​ራም ጋር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ክ​ዓ​ብን ቤት ያጠፋ ዘንድ ወደ ቀባው ወደ ናሚሲ ልጅ ወደ ኢዩ ወጣ።


በለኪሶ የምትቀመጪ ሆይ፥ ሰረገላውን ለፈረስ እሰሪ፥ እርስዋ ለጽዮን ሴት ልጆች የኃጢአት መጀመሪያ ነበረች፥ የእስራኤል በደል በአንቺ ዘንድ ተገኝቶአልና።


ወደ ኤል​ዛ​ቤ​ልም፥ “ናቡቴ በድ​ን​ጋይ ተደ​ብ​ድቦ ሞተ” ብለው ላኩ።


ሙሴም ከቃ​ዴስ ወደ ኤዶ​ም​ያስ ንጉሥ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን እን​ዲህ ብሎ ላከ፥ “ወን​ድ​ምህ እስ​ራ​ኤል እን​ዲህ ይላል፦ ያገ​ኘ​ንን መከራ ሁሉ አንተ ታው​ቃ​ለህ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች