Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 9:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እነ​ር​ሱም፥ “ዋሸ​ኸን፤ ነገር ግን ንገ​ረን” አሉት፤ ኢዩም፦ ለጌ​ታው ልጆች፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባ​ሁህ ብሎ እን​ዲ​ህና እን​ዲህ ነገ​ረኝ” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እነርሱም፣ “ይህማ ትክክል አይደለም፤ ይልቅስ እውነቱን ንገረን” አሉት። ኢዩም እንዲህ አለ፤ “እርሱ የነገረኝማ ይህ ነው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የእስራኤል ንጉሥ እንድትሆን ቀብቼሃለሁ።’ ”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እነርሱም “ኧረ እኛ አናውቅም፤ ምን እንደ ተናገረ አስረዳን!” ሲሉ መለሱለት። ኢዩም፦ “‘በእስራኤል ላይ ተቀብተህ እንድትነግሥ እግዚአብሔር አዞአል’ አለኝ” ሲል አስረዳቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እነርሱም “ኧረ እኛ አናውቅም፤ ምን እንደ ተናገረ አስረዳን!” ሲሉ መለሱለት። ኢዩም፦ “ ‘በእስራኤል ላይ ተቀብተህ እንድትነግሥ እግዚአብሔር አዞአል’ አለኝ” ሲል አስረዳቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እነርሱም “ሐሰት ነው፤ ያለውን ንገረን፤” አሉት፤ እርሱም “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባሁህ፤’ ብሎ እንዲህ እንዲህ ነገረኝ፤” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 9:12
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢዩም ወደ ጌታው ብላ​ቴ​ኖች ወጣ፤ እነ​ር​ሱም፥ “ደኅና ነውን? ይህ እብድ ለምን ወደ አንተ መጣ?” አሉት። እር​ሱም፥ “ሰው​ዬው ፌዝ እን​ደ​ሚ​ና​ገር አታ​ው​ቁ​ምን?” አላ​ቸው።


በሰ​ሙም ጊዜ ሁሉም ፈጥ​ነው ልብ​ሳ​ቸ​ውን ወሰዱ፤ በሰ​ገ​ነቱ መውጫ እር​ከን ላይም ከእ​ግሩ በታች አነ​ጠ​ፉት፥ መለ​ከ​ትም እየ​ነፉ፥ “ኢዩ ነግ​ሦ​አል” አሉ።


ሳሙ​ኤ​ልም የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ወስዶ በራሱ ላይ አፈ​ሰ​ሰው፤ ሳመ​ውም፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “በሕ​ዝቡ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ትነ​ግሥ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀብ​ቶ​ሃል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሕዝብ ትገ​ዛ​ለህ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ካሉ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ ታድ​ና​ቸ​ዋ​ለህ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በር​ስቱ ላይ ትነ​ግሥ ዘንድ እንደ ቀባህ ምል​ክቱ ይህ ነው።


በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ የና​ሚ​ሶን ልጅ ኢዩን ቅባው፤ በፋ​ን​ታ​ህም ነቢይ ይሆን ዘንድ የአ​ቤ​ል​መ​ሁ​ላን ሰው የሣ​ፋ​ጥን ልጅ ኤል​ሳ​ዕን ቅባው፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች