Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 8:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ንጉ​ሡም ኢዮ​ራም ከሶ​ርያ ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል ጋር በተ​ዋጋ ጊዜ ሶር​ያ​ው​ያን በሬ​ማት ያቈ​ሰ​ሉ​ትን ቍስል ይታ​ከም ዘንድ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ተመ​ለሰ። የአ​ክ​ዓ​ብም ልጅ ኢዮ​ራም ታምሞ ነበ​ርና የኢ​ዮ​ራም ልጅ አካ​ዝ​ያስ ሊያ​የው ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ወረደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ስለዚህ ንጉሥ ኢዮራም፣ ከአዛሄል ጋራ ራማት ላይ ባደረገው ጦርነት ሶርያውያን ካቈሰሉት ቍስል ለመዳን ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ። ከዚያም የአክዓብ ልጅ ኢዮራም ስለ ታመመ፣ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራሆም ልጅ አካዝያስ ሊጠይቀው ወደ ኢይዝራኤል ወረደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ኢዮራምም ከንጉሥ አዛሄል ጋር ሆኖ በሬማት በተደረገው ጦርነት የደረሰበትን ቁስል ለመፈወስ ወደ ኢይዝራኤል ከተማ ተመለሰ። የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በደረሰበት ጉዳት እርሱን ለመጠየቅ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ሊጠይቀው ወደ ኢይዝራኤል ከተማ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ኢዮራምም ከንጉሥ ኣዛሄል ጋር ሆኖ በሬማት በተደረገው ጦርነት የደረሰበትን ቊስል ለመፈወስ ወደ ኢይዝራኤል ከተማ ተመለሰ። የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በደረሰበት ጒዳት እርሱን ለመጠየቅ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ሊጠይቀው ወደ ኢይዝራኤል ከተማ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ንጉሡም ኢዮራም ከሶርያ ንጉሥ ከአዛሄል ጋር በተዋጋ ጊዜ ሶርያውያን በሬማት ያቈሰሉትን ቈስል ይታከም ዘንድ ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ። የአክዓብም ልጅ ኢዮራም ታምሞ ነበርና የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ሊያየው ወደ ኢይዝራኤል ወረደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 8:29
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከአ​ክ​ዓ​ብም ልጅ ከኢ​ዮ​ራም ጋር የሶ​ር​ያን ንጉሥ አዛ​ሄ​ልን በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ ሊጋ​ጠም ሄደ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ኢዮ​ራ​ምን አቈ​ሰ​ሉት።


አንድ ሰውም ቀስ​ቱን ድን​ገት ገትሮ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ በሳ​ን​ባ​ውና በደ​ረቱ መካ​ከል ወጋው፤ ሰረ​ገ​ለ​ኛ​ው​ንም፥ “መል​ሰህ ንዳ፤ ተወ​ግ​ቻ​ለ​ሁና ከሰ​ልፍ ውስጥ አው​ጣኝ” አለው።


ነቢ​ዩም ኤል​ሳዕ ከነ​ቢ​ያት ልጆች አን​ዱን ጠርቶ እን​ዲህ አለው፥ “ወገ​ብ​ህን ታጥ​ቀህ ይህን የዘ​ይት ቀንድ በእ​ጅህ ያዝ፤ ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓ​ድም ሂድ።


ኢዩ ከይ​ሁዳ ንጉሥ ከአ​ካ​ዝ​ያስ ወን​ድ​ሞች ጋር ተገ​ና​ኝቶ፥ “እና​ንተ እነ​ማን ናችሁ?” አለ፤ እነ​ር​ሱም፥ “እኛ የይ​ሁዳ ንጉሥ የአ​ካ​ዝ​ያስ ወን​ድ​ሞች ነን፤ የን​ጉ​ሡ​ንና የእ​ቴ​ጌ​ዪ​ቱን ልጆች ደኅ​ን​ነት እን​ነ​ግ​ረው ዘንድ ወረ​ድን” አሉት።


ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ኢይ​ዝ​ራ​ኤል፥ ከል​ሰ​ሉት፥ ሱሳን፤


እን​ዲ​ሁም የና​ሜሲ ልጅ የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ልጅ ኢዩ ኢዮ​ራ​ምን ከዳው። ኢዮ​ራ​ምና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ከሶ​ርያ ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል የተ​ነሣ ሬማት ዘገ​ለ​ዓ​ድን ይጠ​ብቁ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች