Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 7:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ንጉ​ሡም በሌ​ሊት ተነ​ሥቶ ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “ሶር​ያ​ው​ያን ያደ​ረ​ጉ​ብ​ንን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ እንደ ተራ​ብን ያው​ቃሉ፤ ስለ​ዚህ፦ ከከ​ተ​ማ​ይቱ በወጡ ጊዜ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው እን​ይ​ዛ​ቸ​ዋ​ለን፤ ወደ ከተ​ማም እን​ገ​ባ​ለን ብለው በሜዳ ይሸ​ሸጉ ዘንድ ከሰ​ፈሩ ወጥ​ተ​ዋል” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ንጉሡም በሌሊት ተነሥቶ ለጦር አለቆቹ እንዲህ አላቸው፤ “ሶርያውያን ያደረጉብንን እነግራችኋለሁ፤ መራባችንን ስለሚያውቁ፣ ‘መቼም መውጣታቸው አይቀርም፤ ከዚያም ከነሕይወታቸው እንማርካቸዋለን፤ እኛም ሰተት ብለን ወደ ከተማዪቱ እንገባለን’ በማለት በገጠር ለመደበቅ ከሰፈራቸው ወጥተዋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ጊዜውም ገና ሌሊት ነበር፤ ንጉሡ ግን ከመኝታው ተነሥቶ ባለሟሎቹ የሆኑትን ባለ ሥልጣኖች እንዲህ አላቸው፤ “የሶርያውያንን ዕቅድ ልንገራችሁ! እነርሱ በዚህ ስላለው ራብ ያውቃሉ፤ ስለዚህ ሰፈራቸውን ለቀው በገጠር ለመሸሸግ ሄደዋል፤ እኛም ምግብ ፍለጋ ብንወጣ ከነሕይወታችን ማርከው ከተማችንን ይወስዳሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ጊዜውም ገና ሌሊት ነበር፤ ንጉሡ ግን ከመኝታው ተነሥቶ ባለሟሎቹ የሆኑትን ባለሥልጣኖች እንዲህ አላቸው፤ “የሶርያውያንን ዕቅድ ልንገራችሁ! እነርሱ በዚህ ስላለው ራብ ያውቃሉ፤ ስለዚህ ሰፈራቸውን ለቀው በገጠር ለመሸሸግ ሄደዋል፤ እኛም ምግብ ፍለጋ ብንወጣ ከነሕይወታችን ማርከው ከተማችንን ይወስዳሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ንጉሡም በሌሊት ተነሥቶ ባሪያዎቹን “ሶርያውያን ያደረጉብንን እነግራችኋለሁ፤ እንደ ተራብን ያውቃሉ፤ ስለዚህ ‘ከከተማይቱ በወጡ ጊዜ በሕይወታቸው እንይዛቸዋለን፤ ወደ ከተማም እንገባለን፤’ ብለው በሜዳ ይሸሸጉ ዘንድ ከሰፈሩ ወጥተዋል፤” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 7:12
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የደ​ጁም ጠባ​ቂ​ዎች ለን​ጉሡ ይነ​ግሩ ዘንድ ወደ ውስጥ ገቡ፤ ለን​ጉ​ሡም ቤት አወሩ።


ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አንዱ መልሶ፥ “እዚህ ከቀ​ሩት ፈረ​ሶች አም​ስት ይው​ሰዱ፤ እነሆ፥ እነ​ርሱ በቀ​ሩት በእ​ስ​ራ​ኤል ቍጥር ናቸው፥ እን​ስ​ደ​ድና ይዩ” አለ።


እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “እነሆ፥ ሂዱና ከከ​ተ​ማ​ዪቱ በስ​ተ​ኋላ ተደ​በቁ፤ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ አት​ራቁ፤ ሁላ​ች​ሁም ተዘ​ጋ​ጅ​ታ​ችሁ ተቀ​መጡ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች