Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 6:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ የሴ​ቲ​ቱን ቃል ሰምቶ ልብ​ሱን ቀደደ፤ በቅ​ጥ​ርም ይመ​ላ​ለስ ነበር፤ ሕዝ​ቡም በስ​ተ​ው​ስጥ በሥ​ጋው ላይ ለብ​ሶት የነ​በ​ረ​ውን ማቅ አዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ንጉሡም ሴቲቱ ያለችውን ሲሰማ ልብሱን ቀደደ፤ በቅጥሩ ላይ በሚመላለስበትም ጊዜ፣ ማቅ ከውስጥ መልበሱን ሕዝቡ አየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ በኀዘን ልብሱን ቀደደ፤ በግንቡ ላይ በመሆኑ በአቅራቢያው የነበረው ሕዝብ ንጉሡ ከልብሱ በውስጥ በኩል ማቅ ለብሶ እንደ ነበር አዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ በሐዘን ልብሱን ቀደደ፤ በግንቡ ላይ በመሆኑ በአቅራቢያው የነበረው ሕዝብ ንጉሡ ከልብሱ በውስጥ በኩል ማቅ ለብሶ እንደ ነበር አዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ንጉሡም የሴቲቱን ቃል ሰምቶ ልብሱን ቀደደ፤ በቅጥርም ይመላለስ ነበር፤ ሕዝቡም በስተ ውስጥ በሥጋው ላይ ለብሶት የነበረውን ማቅ አዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 6:30
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተቈ​ጠሩ፤ ሊገ​ጥ​ሙ​አ​ቸ​ውም ወጡ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እንደ ሁለት ትና​ንሽ የፍ​የል መን​ጋ​ዎች ሆነው በፊ​ታ​ቸው ሰፈሩ፤ ሶር​ያ​ው​ያን ግን ምድ​ርን ሞል​ተ​ዋት ነበር።


ንጉ​ሡም ሕዝ​ቅ​ያስ ይህን በሰማ ጊዜ ልብ​ሱን ቀደደ፥ ማቅም ለበሰ፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ገባ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ደብ​ዳ​ቤ​ውን ባነ​በበ ጊዜ ልብ​ሱን ቀድዶ፥ “ሰውን ከለ​ምጹ እፈ​ውስ ዘንድ ይህ ሰው ወደ እኔ መስ​ደዱ እኔ በውኑ ለመ​ግ​ደ​ልና ለማ​ዳን የም​ችል አም​ላክ ነኝን? ተመ​ል​ከቱ፥ የጠብ ምክ​ን​ያት እን​ደ​ሚ​ፈ​ል​ግ​ብኝ ተመ​ል​ከቱ” አለ።


የቤቱ አዛዥ የኬ​ል​ቅዩ ልጅ ኤል​ያ​ቄም፥ ጸሓ​ፊው ሳም​ናስ፥ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የአ​ሳፍ ልጅ ዮአስ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀድ​ደው ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ገቡ፥ የራ​ፋ​ስ​ቂ​ስ​ንም ቃል ነገ​ሩት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች