2 ነገሥት 6:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)28 ንጉሡም፥ “ምን ሆነሻል?” አላት፤ እርስዋም፥ “ይህች ሴት፦ ዛሬ እንድንበላው ልጅሽን አምጪ፤ ነገም ልጄን እንበላለን አለችኝ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም28 ከዚያም፣ “ለመሆኑ ችግርሽ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቃት። እርሷም እንዲህ ስትል መለሰችለት፤ “ይህች ሴት፣ ‘ዛሬ እንድንበላው ልጅሽን አምጪው፤ ነገ ደግሞ የእኔን ልጅ እንበላዋለን’ አለችኝ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)28 ለመሆኑ ችግርሽ ምንድነው?” ሲል ጠየቃት። እርሷም እንዲህ ስትል መለሰችለት፤ “ባለፈው ቀን ይህች ሴት ‘ዛሬ የአንቺን ልጅ እንብላ፤ በማግስቱ ደግሞ የእኔን ልጅ እንበላለን’ ስትል ሐሳብ አቀረበች። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም28 ለመሆኑ ችግርሽ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቃት። እርስዋም እንዲህ ስትል መለሰችለት፤ “ባለፈው ቀን ይህች ሴት ‘ዛሬ የአንቺን ልጅ እንብላ፤ በማግስቱ ደግሞ የእኔን ልጅ እንበላለን’ ስትል ሐሳብ አቀረበች። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)28 ንጉሡም “ምን ሆነሻል?” አላት፤ እርስዋም “ይህች ሴት ‘ዛሬ እንድንበላው ልጅሽን አምጪ፤ ነገም ልጄን እንበላለን፤’ አለችኝ። ምዕራፉን ተመልከት |