Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 6:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም አንዱ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ሀገር ነቢዩ ኤል​ሳዕ ያለ አይ​ደ​ለ​ምን? በእ​ል​ፍ​ኝህ ውስጥ ሆነህ የም​ት​ና​ገ​ረ​ው​ንና ቃል​ህን ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እርሱ ይነ​ግ​ረ​ዋል፤” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ከጦር አለቆቹም አንዱ፣ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ፤ ከእኛ በኩል ማንም ሰው የለም፤ ነገር ግን አንተ በእልፍኝህ ሆነህ እንኳ የምትናገረውን አንዲቱም ሳትቀር ለእስራኤል ንጉሥ የሚነግረው በእስራኤል ያለው ነቢዩ ኤልሳዕ ነው” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ከእነርሱም አንዱ “ንጉሥ ሆይ፥ ከእኛ መካከል ይህን የሚያደርግ ማንም የለም፤ በመኝታ ክፍልህ እንኳ ሆነህ የምትናገረውን ሁሉ ሳይቀር ለእስራኤል ንጉሥ ምሥጢሩን የሚገልጥለት ኤልሳዕ የተባለው ነቢይ ነው” ሲል መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከእነርሱም አንዱ “ንጉሥ ሆይ፥ ከእኛ መካከል ይህን የሚያደርግ ማንም የለም፤ በመኝታ ክፍልህ እንኳ ሆነህ የምትናገረውን ሁሉ ሳይቀር ለእስራኤል ንጉሥ ምሥጢሩን የሚገልጥለት ኤልሳዕ የተባለው ነቢይ ነው” ሲል መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ከባሪያዎቹም አንዱ “ጌታዬ ሆይ! እንዲህ እኮ አይደለም፤ ነገር ግን በእልፍኝህ ውስጥ ሆነህ የምትናገረውን በእስራኤል ዘንድ ያለ ነቢይ ኤልሳዕ ለእስራኤል ንጉሥ ይነግረዋል፤” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 6:12
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለባ​ሪ​ያ​ዎቹ ለነ​ቢ​ያት ያል​ገ​ለ​ጠ​ው​ንና ያል​ነ​ገ​ረ​ውን ምንም አያ​ደ​ር​ግ​ምና።


ምክ​ራ​ቸ​ውን ጥልቅ አድ​ር​ገው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ሰ​ውሩ ወዮ​ላ​ቸው! ሥራ​ቸ​ው​ንም በጨ​ለማ ውስጥ አድ​ር​ገው፥ “ማን ያየ​ናል? ወይስ ማን ያው​ቀ​ናል?” ለሚሉ ወዮ​ላ​ቸው!


የሰ​ማይ ዎፍ ቃል​ህን ያወ​ጣ​ዋ​ልና፥ ክንፍ ያለ​ውም ነገ​ር​ህን ያወ​ራ​ዋ​ልና በል​ብህ ዐሳብ እን​ኳን ቢሆን ንጉ​ሥን አት​ሳ​ደብ፥ በመ​ኝታ ቤት​ህም ባለ​ጠ​ጋን አት​ሳ​ደብ።


እመ​ቤ​ቷ​ንም፥ “ጌታዬ በሰ​ማ​ርያ ወደ​ሚ​ኖ​ረው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ ነቢዩ ይሄድ ዘንድ በተ​ገ​ባው ነበር፤ ከለ​ም​ጹም በፈ​ወ​ሰው ነበር” አለ​ቻት።


ኤል​ሳ​ዕም የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ልብ​ሱን እንደ ቀደደ በሰማ ጊዜ፥ “ልብ​ስ​ህን ለምን ቀደ​ድህ? ንዕ​ማን ወደ እኔ ይምጣ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ነቢይ እን​ዳለ ያው​ቃል” ብሎ ወደ ንጉሡ ላከ።


ወን​ዙም ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ችን ያፈ​ላል፤ ወጥ​ተ​ውም ወደ ቤትህ፥ ወደ መኝታ ቤትህ፥ ወደ አል​ጋ​ህም፥ ወደ ሹሞ​ች​ህም ቤት፥ በሕ​ዝ​ብ​ህም ላይ፥ ወደ ቡሃ​ቃ​ዎ​ች​ህም፥ ወደ ምድ​ጃ​ዎ​ች​ህም ይገ​ባሉ፤


የሶ​ር​ያም ንጉሥ መን​ፈስ ስለ​ዚህ እጅግ ተበ​ሳ​ጨች፤ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ጠርቶ፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ማን እን​ደ​ሚ​ነ​ግ​ረው አት​ነ​ግ​ሩ​ኝ​ምን?” አላ​ቸው።


እር​ሱም፥ “ልኬ አስ​ይ​ዘው ዘንድ ሄዳ​ችሁ ወዴት እንደ ሆነ ዕወቁ፤” አለ። እነ​ር​ሱም፥ “እነሆ፥ በዶ​ታ​ይን አለ” ብለው ነገ​ሩት።


እር​ሱም፥ “ያ ሰው ከሰ​ረ​ገ​ላው ወርዶ ሊቀ​በ​ልህ በተ​መ​ለሰ ጊዜ ልቤ ከአ​ንተ ጋር አል​ሄ​ደ​ምን? አሁ​ንም ወር​ቁ​ንና ልብ​ሱን፥ ተቀ​ብ​ለ​ሃል፤ ለወ​ይን ቦታ፥ ለመ​ሰ​ማ​ርያ ቦታና ለዘ​ይት ቦታ፥ ለላ​ሞ​ችና ለበ​ጎች፥ ለወ​ን​ዶ​ችና ለሴ​ቶች ባሮች ይሁ​ንህ።


ጥበብና ብርታት፥ ምክርም፥ በኃጥእ ዘንድ የሉም።


ምክ​ርን ብት​መ​ክ​ሩም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክ​ራ​ች​ሁን ይለ​ው​ጣል፤ የተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁ​ትም ነገር አይ​ሆ​ን​ላ​ች​ሁም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኛ ጋር ነውና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች