Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 5:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ከዚ​ህም በኋላ ገብቶ፥ በጌ​ታው ፊት ቆመ፤ ኤል​ሳ​ዕም፥ “ግያዝ ሆይ፥ ከወ​ዴት መጣህ?” አለው። እር​ሱም፥ “እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ወዴ​ትም አል​ሄ​ድ​ሁም” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ከዚያም ገብቶ በጌታው በኤልሳዕ ፊት ቆመ። ኤልሳዕም፣ “ግያዝ ሆይ፤ የት ነበርህ?” ሲል ጠየቀው። ግያዝም፣ “አገልጋይህ የትም አልሄደም” ብሎ መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ወደ ቤት ተመልሶ ገባ፤ ኤልሳዕም “እስከ አሁን የት ነበርክ?” ሲል ጠየቀው። ግያዝም “ጌታዬ፥ ኧረ እኔ የትም አልሄድኩም” ሲል መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ወደ ቤት ተመልሶ ገባ፤ ኤልሳዕም “እስከ አሁን የት ነበርክ?” ሲል ጠየቀው። ግያዝም “ጌታዬ፥ ኧረ እኔ የትም አልሄድኩም” ሲል መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 እርሱ ግን ገብቶ በጌታው ፊት ቆመ፤ ኤልሳዕም “ግያዝ ሆይ! ከወዴት መጣህ?” አለው። እርሱም “እኔ ባሪያህ ወዴትም አልሄድሁም፤” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 5:25
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እር​ሱም፥ “ሁሉ ደኅና ነው፦ አሁን ከነ​ቢ​ያት ወገን የሆኑ ሁለት ጐል​ማ​ሶች ከተ​ራ​ራ​ማው ከኤ​ፍ​ሬም ሀገር ወደ እኔ መጥ​ተ​ዋ​ልና፤ አንድ መክ​ሊት ብርና ሁለት መለ​ወጫ ልብስ ትሰ​ጣ​ቸው ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ ብሎ ጌታዬ ላከኝ” አለው።


ሲበሉም “እውነት እላችኋለሁ፤ ከእናንተ አንዱ እኔን አሳልፎ ይሰጣል፤” አለ።


ሕዝብ እን​ደ​ሚ​መጣ ወደ አንተ ይመ​ጣሉ፤ እንደ ሕዝ​ቤም በፊ​ትህ ይቀ​መ​ጣሉ፤ ቃል​ህ​ንም ይሰ​ማሉ፤ ነገር ግን አያ​ደ​ር​ጉ​ትም፤ በአ​ፋ​ቸው ሐሰት ነገር አለና፥ ልባ​ቸ​ውም ጣዖ​ታ​ትን ይከ​ተ​ላ​ልና።


ነቢዩ ኢሳ​ይ​ያ​ስም ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ መጥቶ፥ “እነ​ዚህ ሰዎች ምን አሉ? ከወ​ዴ​ትስ ወደ አንተ መጡ?” አለው። ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፥ “ከሩቅ ሀገር ከባ​ቢ​ሎን ወደ እኔ መጡ” አለው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ፥ “የሦራ አገ​ል​ጋይ አጋር ሆይ፥ ከወ​ዴት መጣሽ? ወዴ​ትስ ትሄ​ጂ​ያ​ለሽ?” አላት። እር​ስ​ዋም፥ “እኔ ከእ​መ​ቤቴ ከሦራ ፊት እኰ​በ​ል​ላ​ለሁ” አለች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃየ​ልን አለው፥ “ወን​ድ​ምህ አቤል ወዴት ነው?” ቃየ​ልም አለ፥ “አላ​ው​ቅም፤ በውኑ የወ​ን​ድሜ ጠባ​ቂው እኔ ነኝን?”


ራት ሲበ​ሉም አሳ​ልፎ ይሰ​ጠው ዘንድ በስ​ም​ዖን ልጅ በአ​ስ​ቆ​ሮቱ ሰው በይ​ሁዳ ልብ ሰይ​ጣን አደረ።


ዖዝ​ያ​ንም ተቈጣ፤ በመ​ቅ​ደ​ስም የሚ​ያ​ጥ​ን​በት ጥና በእጁ ነበረ፤ ካህ​ና​ቱ​ንም በተ​ቈጣ ጊዜ በካ​ህ​ናቱ ፊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ በዕ​ጣኑ መሠ​ዊያ አጠ​ገብ ሳለ በግ​ን​ባሩ ላይ ለምጽ ታየ።


ከቤተ ሰቡም አንዱ እር​ሱ​ንና ብላ​ቴ​ና​ውን፥ “ወዴት ሄዳ​ችሁ ኖሮ​አል?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “አህ​ዮ​ችን ልን​ፈ​ልግ ሄደን ነበር፤ ባጣ​ና​ቸ​ውም ጊዜ ወደ ሳሙ​ኤል መጣን” አሉት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች