Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 5:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ንዕ​ማ​ንም፥ “እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀር ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ወይም ሌላ መሥ​ዋ​ዕት አላ​ቀ​ር​ብ​ምና ሁለት የበ​ቅሎ ጭነት አፈር ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ ይስ​ጡት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ንዕማንም እንዲህ አለው፤ “ስጦታውን የማትቀበል ከሆነ፣ ከእግዚአብሔር በቀር ለማንኛውም አምላክ የሚቃጠል ወይም ሌላ መሥዋዕት ስለማላቀርብ፣ ሁለት የበቅሎ ጭነት ዐፈር እንድወስድ ትፈቅድልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ስለዚህም ንዕማን እንዲህ አለ፦ “ስጦታዬን የማትቀበለኝ ከሆነ ከአሁን ጀምሮ ለእግዚአብሔር ብቻ እንጂ ለሌሎች ባዕዳን አማልክት የሚቃጠልም ሆነ ወይም ሌላ ዓይነት መሥዋዕት ስለማላቀርብ የሁለት በቅሎ ጭነት ዐፈር ይዤ እንድሄድ ፍቀድልኝ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ስለዚህም ንዕማን እንዲህ አለ፦ “ስጦታዬን የማትቀበለኝ ከሆነ ከአሁን ጀምሮ ለእግዚአብሔር ብቻ እንጂ ለሌሎች ባዕዳን አማልክት የሚቃጠልም ሆነ ወይም ሌላ ዐይነት መሥዋዕት ስለማላቀርብ የሁለት በቅሎ ጭነት ዐፈር ይዤ እንድሄድ ፍቀድልኝ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ንዕማንም “እኔ ባሪያህ ከእንግዲህ ወዲህ ከእግዚአብሔር በቀር ለሌሎች አማልክት የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ሌላ መሥዋዕት አላቀርብምና ሁለት የበቅሎ ጭነት አፈር እንድወስድ እሺ ትለኝ ዘንድ እለምንሃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 5:17
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይኸ​ውም ዐይ​ና​ቸ​ውን ትከ​ፍ​ት​ላ​ቸው ዘንድ፥ ከጨ​ለ​ማም ወደ ብር​ሃን፥ ሰይ​ጣ​ንን ከማ​ም​ለ​ክም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትመ​ል​ሳ​ቸው ዘንድ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸው ዘንድ፥ በስ​ሜም በማ​መን ከቅ​ዱ​ሳን ጋር አን​ድ​ነ​ትን ያገኙ ዘንድ ነው።’


የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።


እም​ነቱ ደካማ የሆ​ነ​ውን ሰው ታገ​ሡት፤ በዐ​ሳ​ቡም አት​ፍ​ረዱ።


የደ​ማ​ስቆ ወን​ዞች ባብ​ናና ፋርፋ ከእ​ስ​ራ​ኤል ውኆች ሁሉ አይ​ሻ​ሉ​ምን? ሄጄስ በእ​ነ​ርሱ ውስጥ መጠ​መ​ቅና መን​ጻት አይ​ቻ​ለ​ኝም ኖሮ​አ​ልን?” ብሎ በቍጣ ተመ​ልሶ ሄደ።


ከአ​ፈ​ርም መሠ​ዊያ ሥራ​ልኝ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ት​ህን፥ በጎ​ች​ህ​ንም፥ በሬ​ዎ​ች​ህ​ንም ሠዋ​በት፤ ስሜን ባስ​ጠ​ራ​ሁ​በት ስፍራ ሁሉ ወደ አንተ መጥቼ እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ።


እነርሱ ራሳቸው ወደ እናንተ መግባታችን እንዴት እንደነበረ ስለ እኛ ይናገራሉና፤ ለሕያውና ለእውነተኛ አምላክም ታገለግሉ ዘንድ፥ ከሙታንም ያስነሣውን ልጁን እርሱንም ኢየሱስን ከሚመጣው ቍጣ የሚያድነንን ከሰማይ ትጠብቁ ዘንድ፥ ከጣዖቶች ወደ እግዚአብሔር እንዴት እንደተመለሳችሁ ይናገራሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የእ​ኔን የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን ኀጢ​አት በዚህ ነገር ብቻ ይቅር ይበ​ለኝ፤ ጌታዬ በዚያ ይሰ​ግድ ዘንድ እጄን ተደ​ግፎ ወደ ሬማን ቤት በገ​ባና በሰ​ገደ ጊዜ፥ እኔም በሬ​ማን ቤት በሰ​ገ​ድሁ ጊዜ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ነገር እኔን አገ​ል​ጋ​ይ​ህን ይቅር ይለ​ኛል” አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች