Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 4:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 ከዚ​ህም በኋላ ሰዎቹ ይበሉ ዘንድ አቀ​ረ​በ​ላ​ቸው፤ የበ​ሰ​ለ​ው​ንም ቅጠል በሚ​በ​ሉ​በት ጊዜ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሆይ፥ በም​ን​ቸቱ ውስጥ መርዝ አለ” ብለው ጮኹ፤ ይበ​ሉም ዘንድ አል​ቻ​ሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 ሰዎቹ እንዲመገቡትም ወጡ ወጣ፤ ገና አንደ ቀመሱትም፣ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፤ በምንቸቱ ውስጥ የሚገድል መርዝ አለ!” ብለው ጮኹ፤ ሊመገቡትም አልቻሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ነቢያትም እንዲመገቡት የወጣላቸውን ወጥ ቀምሰው “በዚህ ወጥ ውስጥ የሚገድል መርዝ አለ!” ብለው ወደ ኤልሳዕ ጮኹ፤ ሊመገቡትም አልቻሉም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ነቢያትም እንዲመገቡት የወጣላቸውን ወጥ ቀምሰው “በዚህ ወጥ ውስጥ የሚገድል መርዝ አለ!” ብለው ወደ ኤልሳዕ ጮኹ፤ ሊመገቡትም አልቻሉም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ሰዎቹም ይበሉ ዘንድ ቀዱ፤ ወጡንም በቀመሱ ጊዜ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! በምንቸቱ ውስጥ ሞት አለ፤” ብለው ጮኹ፤ ይበሉም ዘንድ አልቻሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 4:40
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እባቦችን ይይዛሉ፤የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጐዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ፤ እነርሱም ይድናሉ።


ወደ ማራም በመጡ ጊዜ ከማራ ውኃ ሊጠጡ አል​ቻ​ሉም፤ ውኃው መራራ ነበ​ርና፤ ስለ​ዚህ የዚያ ስፍራ ስም “መሪር” ተብሎ ተጠራ።


አሁን እን​ግ​ዲህ እን​ደ​ገና በዚህ ጊዜ ብቻ ኀጢ​አ​ቴን ይቅር በሉኝ፤ ይህ​ንም ሞት ብቻ ከእኔ ያነ​ሣ​ልኝ ዘንድ ወደ አም​ላ​ካ​ችሁ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ዩ​ልኝ” አላ​ቸው።


ሴት​ዮ​ዋም ለባ​ልዋ፥ “ይህ በእኛ ዘንድ ሁል​ጊዜ የሚ​ያ​ል​ፈው ቅዱስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ሆነ አው​ቃ​ለሁ።


ንጉ​ሡም ደግሞ ሦስ​ተኛ የአ​ምሳ አለቃ ከአ​ምሳ ሰዎች ጋር ላከ፤ ሦስ​ተ​ኛ​ውም የአ​ምሳ አለቃ ወጥቶ በኤ​ል​ያስ ፊት በጕ​ል​በቱ ተን​በ​ረ​ከ​ከና ለመ​ነው እን​ዲ​ህም አለው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሆይ! ሰው​ነ​ቴና የእ​ነ​ዚህ የአ​ም​ሳው ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ሰው​ነት በፊ​ትህ የከ​በ​ረች ትሁን።


ደግ​ሞም ሌላ የአ​ምሳ አለቃ ከአ​ምሳ ሰዎች ጋር ላከ​በት፤ የአ​ምሳ አለ​ቃ​ውም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሆይ! ንጉሡ፦ ና፤ ፈጥ​ነህ ውረድ ይላል” ብሎ ተና​ገረ።


እር​ስ​ዋም ኤል​ያ​ስን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሆይ፥ እኔ ከአ​ንተ ጋር ምን አለኝ? አን​ተስ ከእኔ ጋር ምን አለህ? ኀጢ​አ​ቴ​ንስ ታሳ​ስብ ዘንድ፥ ልጄ​ንስ ትገ​ድል ዘንድ ወደ እኔ መጥ​ተ​ሃ​ልን?” አለ​ችው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሙሴ ሳይ​ሞት የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች የባ​ረ​ከ​ባት በረ​ከት ይህች ናት።


ንጉ​ሡም ይጠ​ሩት ዘንድ የአ​ምሳ አለ​ቃ​ውን ከአ​ምሳ ሰዎች ጋር ወደ እርሱ ላከ፤ ወደ እር​ሱም ሄዱ፤ እነ​ሆም፥ በተ​ራራ ራስ ላይ ተቀ​ምጦ አገ​ኙት። የአ​ምሳ አለ​ቃ​ውም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሆይ! ንጉሡ ይጠ​ራ​ሃል ፈጥ​ነህ ና፤ ውረድ” አለው።


ለያ​ዕ​ቆ​ብም የም​ስር ንፍሮ ቀቀ​ለ​ች​ለት፤ ዔሳ​ውም ደክሞ ከበ​ረሃ ገባ፤


አን​ዱም ቅጠላ ቅጠል ያመጣ ዘንድ ወደ ሜዳ ወጣ፤ በም​ድረ በዳ​ውም የወ​ይን ቦታ አገኘ፤ ከዚ​ያም የም​ድር ቅጠላ ቅጠል ሰብ​ሰበ፤ ልብ​ሱ​ንም ሞላ፤ መት​ሮም በወጡ ምን​ቸት ውስጥ ጨመ​ረው፤ አበ​ሰ​ለ​ውም፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላ​ወ​ቁም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች