Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 4:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ግያ​ዝ​ንም ጠርቶ፥ “ይህ​ችን ሱማ​ና​ዊት ጥራ” አለው። ጠራ​ትም፤ ወደ እር​ሱም በገ​ባች ጊዜ፥ “ልጅ​ሽን አን​ሥ​ተሽ ውሰጂ” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ኤልሳዕም ግያዝን ጠርቶ፣ “ሱነማዪቱን ጥራት፤” አለው፤ እርሱም ጠራት። እንደ መጣችም፣ “በይ ልጅሽን ውሰጂ” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ኤልሳዕም ግያዝን “ሱነማይቱን ጥራ” አለው፤ እርሷም በመጣች ጊዜ ኤልሳዕ “ልጅሽ ይኸውልሽ!” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ኤልሳዕም ግያዝን “ሱነማይቱን ጥራ” አለው፤ እርስዋም በመጣች ጊዜ ኤልሳዕ “ልጅሽ ይኸውልሽ!” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ግያዝንም ጠርቶ “ይህችን ሱነማዊት ጥራ፤” አለው። ጠራትም፤ ወደ እርሱም በገባች ጊዜ “ልጅሽን አንሥተሽ ውሰጂ፤” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 4:36
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሴቶ​ችም እንደ ትን​ሣኤ ቀን ተነ​ሥ​ተ​ው​ላ​ቸው ሙታ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ተቀ​በሉ፤ ተፈ​ር​ዶ​ባ​ቸው የሞ​ቱም አሉ፤ የም​ት​በ​ል​ጠ​ውን ሕይ​ወት ያገኙ ዘንድ ሊድኑ አል​ወ​ደ​ዱ​ምና።


የሞ​ተ​ውም ተነ​ሥቶ ተቀ​መጠ፤ መና​ገ​ርም ጀመረ፤ ለእ​ና​ቱም ሰጣት።


ኤል​ያ​ስም ብላ​ቴ​ና​ውን ይዞ ከሰ​ገ​ነቱ ወደ ቤት አወ​ረ​ደው፥ ለእ​ና​ቱም ሰጣት፥ “እነሆ፥ ተመ​ል​ከች ልጅሽ ድኖ​አል” አለ።


በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሀገር ሁሉ የተ​ዋ​በች ቆንጆ ፈለጉ፤ ሱነ​ማ​ዪ​ቱን አቢ​ሳ​ንም አገኙ፤ ወደ ንጉ​ሡም ወሰ​ዱ​አት።


ተመ​ል​ሶም በቤቱ ውስጥ አንድ ጊዜ ወዲ​ህና ወዲያ ተመ​ላ​ለሰ፤ ደግ​ሞም ወጥቶ ሰባት ጊዜ በሕ​ፃኑ ላይ ተጋ​ደመ፤ ከዚ​ያም በኋላ ሕፃኑ ዐይ​ኖ​ቹን ከፈተ።


ሴት​ዮ​ዋም ገብታ በእ​ግሩ አጠ​ገብ ወደ​ቀች በም​ድ​ርም ላይ ሰገ​ደች፤ ልጅ​ዋ​ንም አን​ሥታ ወጣች።


እር​ሱም፥ “እነሆ፥ ምሳ​ርህ ውሰ​ደው” አለ፤ እጁ​ንም ዘር​ግቶ ወሰ​ደው።


ኤል​ሳ​ዕም ልጅ​ዋን ያስ​ነ​ሣ​ላ​ትን ሴት፥ “አንቺ ከቤተ ሰብሽ ጋር ተነ​ሥ​ተሽ ሂጂ፤ በም​ታ​ገ​ኚ​ውም ስፍራ ተቀ​መጪ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ራብን ጠር​ቶ​አ​ልና፤ ሰባት ዓመ​ትም በም​ድር ላይ ይቆ​ያል” ብሎ ተና​ገ​ራት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች