Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 3:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ከዚህ በኋላ በእ​ርሱ ፋንታ ንጉሥ የሚ​ሆ​ነ​ውን የበ​ኵር ልጁን ወስዶ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በቅ​ጥሩ ላይ አቀ​ረ​በው። እስ​ራ​ኤ​ልም ታላቅ ጸጸት ተጸ​ጸቱ፤ ከዚ​ያም ርቀው ወደ ምድ​ራ​ቸው ተመ​ለሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ከዚያም በእግሩ ተተክቶ የሚነግሠውን፣ የበኵር ልጁን ወስዶ በከተማዪቱ ቅጥር ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቀረበው። በእስራኤልም ላይ ታላቅ ቍጣ ሆነ፤ ከዚያም ለቅቀው ወደ ገዛ ምድራቸው ተመለሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ስለዚህም በእርሱ ምትክ መንገሥ የሚገባውን የመጀመሪያ ልጁን በከተማይቱ ግንብ ላይ ለሞዓብ አምላክ መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ እስራኤላውያንም በነገሩ ስለ ተሠቀቁ ከተማይቱን ለቀው ወደ አገራቸው ተመለሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ስለዚህም በእርሱ ምትክ መንገሥ የሚገባውን የመጀመሪያ ልጁን በከተማይቱ ግንብ ላይ ለሞአብ አምላክ መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ እስራኤላውያንም በነገሩ ስለ ተሠቀቁ ከተማይቱን ለቀው ወደ አገራቸው ተመለሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 በዚያም ጊዜ በእርሱ ፋንታ ንጉሥ የሚሆነውን የበኵር ልጁን ወስዶ ለሚቃጠል መሥዋዕት በቅጥሩ ላይ አቀረበው። በእስራኤልም ዘንድ ታላቅ ቍጣ ሆነ፤ ከዚያም ርቀው ወደ ምድራቸው ተመለሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 3:27
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔርስ በሺህ አውራ በጎች ወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋልን? ወይስ የበኵር ልጄን ስለ በደሌ፥ የሆዴንም ፍሬ ስለ ነፍሴ ኃጢአት እሰጣለሁን?


ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ አታ​ድ​ርግ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው በእ​ሳት ስለ​ሚ​ያ​ቃ​ጥሉ አሕ​ዛብ ለአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ርኩስ ነገር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጠ​ላ​ልና።


ከአ​ሞን ልጆች ዘንድ በደ​ኅና በተ​መ​ለ​ስሁ ጊዜ፥ ከቤቴ ደጅ ወጥቶ የሚ​ቀ​በ​ለ​ኝን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ” ብሎ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስእ​ለት ተሳለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የኤ​ዶ​ም​ያ​ስን ንጉሥ አጥ​ንት አመድ እስ​ኪ​ሆን ድረስ አቃ​ጥ​ሎ​ታ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የሞ​ዓብ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።


ለእ​ኔም የወ​ለ​ድ​ሻ​ቸ​ውን ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ሽን ወስ​ደሽ መብል ይሆኑ ዘንድ ሠዋ​ሽ​ላ​ቸው፤ ገደ​ል​ሻ​ቸ​ውም።


ሁለት ወርም ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ ወደ አባቷ ተመ​ለ​ሰች፤ ዮፍ​ታ​ሔም የተ​ሳ​ለ​ውን ስእ​ለት አደ​ረገ፤ እር​ስ​ዋም ወንድ አላ​ወ​ቀ​ችም ነበር።


አብ​ር​ሃ​ምም ዐይ​ኖ​ቹን አቅ​ንቶ በተ​መ​ለ​ከተ ጊዜ፥ በኋ​ላው እነሆ፥ አንድ በግ ቀን​ዶቹ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ፤ አብ​ር​ሃ​ምም ሄዶ በጉን ወሰ​ደው፤ በልጁ በይ​ስ​ሐቅ ፈን​ታም ሠዋው።


“የም​ት​ወ​ድ​ደ​ውን አንድ ልጅ​ህን ይስ​ሐ​ቅን ይዘህ ወደ ከፍ​ተ​ኛው ተራራ ሂድ፤ እኔም በም​ነ​ግ​ርህ በአ​ንድ ተራራ ላይ በዚያ መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገህ ሠዋው” አለው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ስለ አክዓብ ወደ ባሪ​ያው ወደ ኤል​ያስ መጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፦


ሁለ​ቱም የዐ​መፅ ልጆች የሆኑ ሰዎች ገብ​ተው በፊቱ ቆሙ፤ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ንጉ​ሡን ሰድ​በ​ሃል” ብለው መሰ​ከ​ሩ​በት። የዚያ ጊዜም ከከ​ተማ አው​ጥ​ተው በድ​ን​ጋይ ደብ​ድ​በው ገደ​ሉት።


የሞ​ዓ​ብም ንጉሥ እንደ ገደ​ሉ​አ​ቸ​ውና ድል እን​ደ​ነ​ሡ​አ​ቸው ባየ ጊዜ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ሰባት መቶ ሰዎ​ችን ከእ​ርሱ ጋር ወሰደ፤ ወደ ኤዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ ያልፉ ዘንድ ሞከሩ፤ አል​ቻ​ሉ​ምም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች