Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 25:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የአ​በ​ዛ​ዎ​ችም አለቃ ታላ​ቁን ካህን ሠራ​ያን ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ካህን ሶፎ​ን​ያ​ስን ሦስ​ቱ​ንም በረ​ኞች ማርኮ ወሰደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 የክብር ዘበኞቹ አዛዥም ሊቀ ካህኑን ሠራያን፣ በማዕርግ ከርሱ ቀጥሎ ያለውን ካህኑን ሶፎንያስንና ሦስቱን የበር ጠባቂዎች እስረኛ አድርጎ ወሰዳቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 የሠራዊቱ አዛዥ ናቡዛርዳን ሊቀ ካህናቱን ሤራያን በማዕረግ የእርሱ ምክትል የሆነውን ካህኑን ሶፎንያስና ሦስቱን የቤተ መቅደስ ዘበኞች እስረኛ አድርጎ ወሰዳቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 የሠራዊቱ አዛዥ ናቡዛርዳን ሊቀ ካህናቱን ሤራያን በማዕርግ የእርሱ ምክትል የሆነውን ካህኑን ሶፎንያስና ሦስቱን የቤተ መቅደስ ዘበኞች እስረኛ አድርጎ ወሰዳቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 የዘበኞቹም አለቃ ታላቁን ካህን ሠራያን፥ ሁለተኛውንም ካህን ሶፎንያስን፥ ሦስቱንም በረኞች ወሰደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 25:18
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉ​ሡም የካ​ህ​ና​ቱን አለቃ ኬል​ቅ​ያ​ስን በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም መዓ​ርግ ያሉ​ትን ካህ​ናት በረ​ኞ​ቹ​ንም፥ ለበ​ዓ​ልና ለማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ ለሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ የተ​ሠ​ሩ​ትን ዕቃ​ዎች ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ ያወጡ ዘንድ አዘ​ዛ​ቸው፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ውጭ በቄ​ድ​ሮን ሜዳ አቃ​ጠ​ሉት፤ አመ​ዱ​ንም ወደ ቤቴል ወሰ​ዱት።


ዓዛ​ር​ያ​ስም ሠራ​ያን ወለደ፤ ሠራ​ያም ኢዮ​ሴ​ዴ​ቅን ወለደ፤


ከዚ​ህም ነገር በኋላ በፋ​ርስ ንጉሥ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ መን​ግ​ሥት ዕዝራ የሠ​ራያ ልጅ፥ የዓ​ዛ​ር​ያስ ልጅ፥ የኬ​ል​ቅ​ያስ ልጅ፥


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የተ​ሾ​መው አለቃ የካ​ህኑ የኢ​ሜር ልጅ ጳስ​ኮር ኤር​ም​ያስ በዚህ ነገር ትን​ቢት ሲና​ገር ሰማ።


የይ​ሁዳ ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ የመ​ል​ክ​ያን ልጅ ጳስ​ኮ​ር​ንና የካ​ህ​ኑን የመ​ዕ​ሴ​ይን ልጅ ሶፎ​ን​ያ​ስን ወደ ኤር​ም​ያስ በላከ ጊዜ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦ እን​ዲ​ህም አለ፦


ከዚህ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስ​ንና አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ ከቸ​ነ​ፈ​ርና ከሰ​ይፍ፥ ከራ​ብም በዚ​ህች ከተማ የቀ​ሩ​ትን ሕዝ​ቡ​ንም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ፥ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም በሚ​ሹት እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም በሰ​ይፍ ስለት ይመ​ታ​ቸ​ዋል፤ አያ​ዝ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ራ​ራ​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ም​ራ​ቸ​ውም።”


“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አለው ሕዝብ ሁሉ፥ ወደ ካህ​ኑም ወደ ማሴው ልጅ ወደ ሶፎ​ን​ያስ፥ ወደ ካህ​ና​ቱም ሁሉ ደብ​ዳ​ቤ​ዎ​ችን በስሜ እን​ዲህ ስትል ልከ​ሃል፦


ካህ​ኑም ሶፎ​ን​ያስ ይህን ደብ​ዳቤ በነ​ቢዩ በኤ​ር​ም​ያስ ጆሮ አነ​በ​በው።


የይ​ሁ​ዳ​ንም ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስ​ንና መኳ​ን​ን​ቱን ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም ለሚ​ሹ​አት እጅ ከእ​ና​ን​ተም ለተ​መ​ለ​ሱት ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ሠራ​ዊት እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ።


የአ​ዛ​ዦ​ቹም አለቃ ታላ​ቅን ካህን ሠራ​ያን፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ካህን ሶፎ​ን​ያ​ስን፥ ሦስ​ቱ​ንም በረ​ኞች ወሰደ፤


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በመ​ካ​ከ​ልዋ ያኖ​ራ​ች​ኋ​ቸው ግዳ​ዮ​ቻ​ችሁ እነ​ርሱ ሥጋ ናቸው፤ ይህ​ችም ከተማ ድስት ናት፤ እና​ን​ተን ግን ከመ​ካ​ከ​ልዋ አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ።


ከባቢሎን ከመጡት ምርኮኞች ከሔልዳይና ከጦብያ ከዮዳኤም ውሰድ፣ በዚያም ቀን መጥተህ ወደ ሶፎንያስ ልጅ ወደ ኢዮስያስ ቤት ግባ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች