Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 25:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የአ​በ​ዛ​ዎች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳ​ንም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ውስጥ የቀ​ረ​ውን ሕዝብ፥ ሸሽ​ተ​ውም ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ የተ​ጠ​ጉ​ትን፥ የቀ​ሩ​ት​ንም ሕዝብ ሁሉ ማርኮ ወሰደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የክብር ዘቡ አዛዥ ናቡዘረዳን ድኾችንና በከተማዪቱ የቀረውን ሕዝብና ሸሽተው ወደ ባቢሎን ንጉሥ የተጠጉትን አፈለሳቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ከዚህም በኋላ ናቡዛርዳን በከተማይቱ ቀርተው የነበሩትንና ሌሎችን ሰዎች፥ እንዲሁም ከድተው ወደ ባቢሎናውያን የተጠጉትን ሁሉ ይዞ ወደ ባቢሎን አጋዛቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ከዚህም በኋላ ናቡዛርዳን በከተማይቱ ቀርተው የነበሩትንና ሌሎችን ሰዎች፥ እንዲሁም ከድተው ወደ ባቢሎናውያን የተጠጉትን ሁሉ ይዞ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን በከተማይቱ ውስጥ የቀረውን ሕዝብ፥ ሸሽተውም ወደ ባቢሎን ንጉሥ የተጠጉትን፥ የቀሩትንም ሕዝብ አፈለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 25:11
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የተ​ረ​ፉ​ት​ንም ወደ ባቢ​ሎን ማረ​ካ​ቸው፤ የሜ​ዶ​ንም ንጉሥ እስ​ኪ​ነ​ግሥ ድረስ ለን​ጉ​ሡና ለል​ጆቹ ባሪ​ያ​ዎች ሆኑ፤


የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ወደ ባቢ​ሎን ከማ​ረ​ካ​ቸው ምር​ኮ​ኞች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና ወደ ይሁዳ፥ ወደ እየ​ከ​ተ​ማ​ቸው የተ​መ​ለ​ሱት የሀ​ገር ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቃሉ ሁሉ የታ​መነ ነው፥ በሥ​ራ​ውም ሁሉ ጻድቅ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ፍ​ገ​መ​ገ​ሙ​ትን ሁሉ ይደ​ግ​ፋ​ቸ​ዋል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የወ​ደ​ቁ​ትን ያነ​ሣ​ቸ​ዋል።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ይችን ከተማ ለከ​ለ​ዳ​ው​ያን እጅና ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ለና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ እር​ሱም ይይ​ዛ​ታል።


የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳ​ንም በከ​ተ​ማ​ዪቱ የቀ​ሩ​ትን ሕዝብ፥ ኰብ​ል​ለ​ውም ወደ እርሱ የገ​ቡ​ትን ሰዎ​ችና የቀ​ረ​ው​ንም የሕ​ዝ​ቡን ቅሬታ ወደ ባቢ​ሎን ማረ​ካ​ቸው።


በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በዐ​ሥራ ዘጠ​ነ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ፊት የሚ​ቆ​መው የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ።


የአ​ዛ​ዦ​ቹም አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን የሕ​ዝ​ቡን ድኆች፥ በከ​ተ​ማም ውስጥ የቀ​ረ​ውን ሕዝብ፥ ሸሽ​ተ​ውም ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ የተ​ጠ​ጉ​ትን፥ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ቅሬታ አመጣ።


በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በሃያ ሦስ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የአ​ዛ​ዦቹ አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ከአ​ይ​ሁድ ሰባት መቶ አርባ አም​ስት ነፍስ ማር​ኮ​አል፤ ሰዎ​ችም ሁሉ አራት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበሩ።


ደግ​ሞም፦ እኔ ምል​ክ​ታ​ችሁ ነኝ፤ እኔ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ እን​ዲሁ ይደ​ረ​ግ​ባ​ቸ​ዋል፥ እነ​ር​ሱ​ንም ማር​ከው ይወ​ስ​ዷ​ቸ​ዋል በል።


ያመ​ለ​ጡ​ትም ሁሉ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ የቀ​ሩ​ትም ሁሉ ወደ እየ​ነ​ፋ​ሳቱ ይበ​ተ​ናሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ርሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


የእ​ስ​ራ​ት​ህም ወራት በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ በከ​ተ​ማ​ዪቱ መካ​ከል ሢሶ​ውን በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ሢሶ​ው​ንም ወስ​ደህ ዙሪ​ያ​ውን በጎ​ራዴ ትመ​ታ​ለህ፤ ሢሶ​ው​ንም ወደ ነፋስ ትበ​ት​ና​ለህ፤ እኔም በኋ​ላ​ቸው ጎራዴ እመ​ዝ​ዛ​ለሁ።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አን​ተን፥ በአ​ን​ተም ላይ የም​ት​ሾ​ማ​ቸ​ውን አለ​ቆ​ች​ህን አን​ተና አባ​ቶ​ችህ ወዳ​ላ​ወ​ቃ​ች​ኋ​ቸው ሕዝብ ይወ​ስ​ድ​ሃል፤ በዚ​ያም ሌሎ​ችን የእ​ን​ጨ​ትና የድ​ን​ጋይ አማ​ል​ክ​ትን ታመ​ል​ካ​ለህ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች