Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 22:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በን​ጉ​ሡም በኢ​ዮ​ስ​ያስ በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በስ​ም​ን​ተ​ኛው ወር ንጉሡ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ጸሓፊ የሜ​ሱ​ላ​ምን ልጅ የኤ​ሴ​ል​ዩን ልጅ ሳፋ​ንን እን​ዲህ ሲል ላከው፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በዘመነ መንግሥቱ በዐሥራ ስምንተኛውም ዓመት ኢዮስያስ የሜሶላምን የልጅ ልጅ የኤዜልያስን ልጅ ጸሓፊውን ሳፋንን ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ላከው፤ እንዲህም አለው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት የመሹላም የልጅ ልጅ፥ የአጻልያ ልጅ የሆነውን የቤተ መንግሥቱ ጸሐፊ ሳፋንን ከዚህ የሚከተለውን መልእክት ወደ ቤተ መቅደስ ላከው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት የመሹላም የልጅ ልጅ፥ የአጻልያ ልጅ የሆነውን የቤተ መንግሥቱ ጸሐፊ ሳፋንን ከዚህ የሚከተለውን መልእክት ወደ ቤተ መቅደስ ላከው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በንጉሡም በኢዮስያስ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት በስምንተኛው ወር ንጉሡ ጸሐፊውን የሜሶላምን ልጅ የኤዜልያስን ልጅ ሳፋንን ወደ እግዚአብሔር ቤት ላከው፤ እንዲህም አለው

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 22:3
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሣ​ጥ​ኑም ውስጥ የተ​ገ​ኘው ወርቅ ብዙ እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ የን​ጉሡ ጸሓ​ፊና የካ​ህ​ናቱ አለቃ ይመጡ ነበር፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የተ​ገ​ኘ​ውን ገን​ዘብ ሁሉ ቈጥ​ረው በከ​ረ​ጢት ውስጥ ያኖ​ሩት ነበር።


ነገር ግን በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመት ይህ ፋሲካ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተደ​ረገ።


በይ​ሁዳ ንጉሥ በአ​ሞጽ ልጅ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ዘመን በመ​ን​ግ​ሥቱ በዐ​ሥራ ሦስ​ተ​ኛው ዓመት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል መጣ​ለት።


ባሮ​ክም የኤ​ር​ም​ያ​ስን ቃል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በላ​ይ​ኛው አደ​ባ​ባይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በአ​ዲሱ በር መግ​ቢያ ባለው በጸ​ሓ​ፊው በሳ​ፋን ልጅ በገ​ማ​ርያ ክፍል በሕ​ዝቡ ሁሉ ጆሮ በመ​ጽ​ሐፉ አን​በበ።


የሳ​ፋ​ንም ልጅ የገ​ማ​ርያ ልጅ ሚክ​ያስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሁሉ ከመ​ጽ​ሐፉ ሰማ።


ወደ ንጉ​ሡም ቤት ወደ ጸሓ​ፊው ክፍል ወረደ፤ እነ​ሆም አለ​ቆቹ ሁሉ፥ ጸሓ​ፊው ኤሊ​ሳማ፥ የሸ​ማያ ልጅ ድላያ፥ የዓ​ክ​ቦር ልጅ ኤል​ና​ታን፥ የሳ​ፋን ልጅ ገማ​ርያ፥ የሐ​ና​ንያ ልጅ ሴዴ​ቅ​ያስ፥ አለ​ቆ​ቹም ሁሉ በዚያ ተቀ​ም​ጠው ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች