Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 21:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ከግ​ብፅ ከአ​ወ​ጣ​ኋ​ቸው ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በፊቴ ክፉ ሠር​ተ​ዋ​ልና፥ አስ​ቈ​ጥ​ተ​ው​ኝ​ማ​ልና።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ይህን የማደርገውም የቀድሞ አባቶቻቸው ከግብጽ ምድር ከወጡበት ጊዜ አንሥቶ እስከ ዛሬ ድረስ በፊቴ ክፉ ድርጊት ስለ ፈጸሙና ለቍጣ ስላነሣሡኝ ነው።’ ”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በእነርሱም ላይ ይህን ሁሉ የማደርግበት ምክንያት የቀድሞ አባቶቻቸው ከግብጽ ከወጡበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ ኃጢአት ሠርተው እኔን በማሳዘናቸውና ቁጣዬን በማነሣሣታቸው ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በእነርሱም ላይ ይህን ሁሉ የማደርግበት ምክንያት የቀድሞ አባቶቻቸው ከግብጽ ከወጡበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ ኃጢአት ሠርተው እኔን በማሳዘናቸውና ቊጣዬን በማነሣሣታቸው ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 አባቶቻቸው ከግብጽ ከወጡ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በፊቴ ክፉ ሠርተዋልና፤ አስቈጥተውኝማልና።’”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 21:15
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሕ​ዝ​ቡ​ንም ቅሬታ እጥ​ላ​ለሁ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ምር​ኮና ብዝ​በዛ ይሆ​ናሉ፤


ደግ​ሞም ምናሴ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይ​ኖች ፊት ክፉ ይሠራ ዘንድ ይሁ​ዳን ካሳ​ተ​በት ኀጢ​አት ሌላ ከዳር እስከ ዳር ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን እስ​ኪ​ሞ​ላት ድረስ እጅግ ብዙ ንጹሕ ደምን አፈ​ሰሰ።


ምድ​ርም በሚ​ቀ​መ​ጡ​ባት ሰዎች ምክ​ን​ያት በደ​ለች፤ ሕጉን ተላ​ል​ፈ​ዋ​ልና፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ለው​ጠ​ዋ​ልና፥ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙ​ንም ቃል ኪዳን አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና።


የይ​ሁዳ ንጉሥ የሕ​ዝ​ቅ​ያስ ልጅ ምናሴ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስለ አደ​ረ​ገው ሁሉ በም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ መካ​ከል ለመ​ከራ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ለእ​ና​ንተ ጕዳት እን​ዲ​ሆን በእ​ጃ​ችሁ ሥራ ታስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሄ። ስለ ኀጢ​አቷ ብዛት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዋ​ር​ዶ​አ​ታ​ልና የሚ​ዘ​ባ​በ​ቱ​ባት በራ​ስዋ ላይ ሆኑ፤ ጠላ​ቶ​ች​ዋም ተደ​ሰቱ፤ ሕፃ​ና​ቶ​ች​ዋም በአ​ስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች ፊት ተማ​ር​ከ​ዋል።


ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት በም​ድረ በዳ በት​እ​ዛዜ ሂዱ አል​ኋ​ቸው፤ አል​ሄ​ዱ​ምም፤ ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው ኖሮ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ት​ንም ሕጌን አፈ​ረሱ፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ፈጽ​መው አረ​ከሱ። በዚ​ህም ጊዜ አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ቍጣ​ዬን በም​ድረ በዳ አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ።


ልጆ​ቻ​ቸው ግን አማ​ረ​ሩኝ፤ ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው ኖሮ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ትን ፍር​ዴን ጠብ​ቀው አላ​ደ​ረ​ጉ​ትም፤ በሥ​ር​ዐ​ቴም አል​ሄ​ዱም፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም አረ​ከሱ፤ በዚ​ህም ጊዜ፦ መዓ​ቴን አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቍጣ​ዬ​ንም በም​ድረ በዳ እፈ​ጽ​ም​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ።


ስለ​ዚህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እን​ዲህ በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እና​ንተ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ኀጢ​አት ረከ​ሳ​ችሁ፤ አመ​ነ​ዘ​ራ​ችሁ፤ ርኵ​ሰ​ታ​ቸ​ው​ንም ተከ​ተ​ላ​ችሁ።


ነገር ግን በቀ​ልን እበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የሰው ልጅ ሆይ! የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ኀጢ​አት አስ​ታ​ው​ቃ​ቸው።


በግ​ብፅ ሀገር አመ​ነ​ዘሩ፤ በኮ​ረ​ዳ​ነ​ታ​ቸው ሳሉ አመ​ነ​ዘሩ፤ በዚ​ያም ጡቶ​ቻ​ቸው ወደቁ፤ በዚ​ያም ድን​ግ​ል​ና​ቸ​ውን አጡ።


እኔ ዐመ​ፃ​ች​ሁ​ንና የአ​ን​ገ​ታ​ች​ሁን ድን​ዳኔ አው​ቃ​ለ​ሁና፤ እኔም ዛሬ ከእ​ና​ንተ ጋር ገና በሕ​ይ​ወት ሳለሁ እና​ንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዐም​ፃ​ች​ኋል፤ ይል​ቁ​ንስ ከሞ​ትሁ በኋላ እን​ዴት ይሆ​ናል?


ከሞ​ትሁ በኋላ ፈጽ​ማ​ችሁ እን​ድ​ት​ረ​ክሱ፥ ካዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁም መን​ገድ ፈቀቅ እን​ድ​ትሉ አው​ቃ​ለ​ሁና። በእ​ጃ​ች​ሁም ሥራ ታስ​ቈ​ጡት ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ስላ​ደ​ረ​ጋ​ችሁ፥ በኋ​ለ​ኛው ዘመን ክፉ ነገር ያገ​ኛ​ች​ኋል።”


ስለ አደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ትም ኀጢ​አት የጥ​ጃ​ውን ምስል ወሰ​ድሁ፤ በእ​ሳ​ትም አቃ​ጠ​ል​ሁት፤ አደ​ቀ​ቅ​ሁ​ትም፤ እንደ ትቢ​ያም እስ​ኪ​ሆን ድረስ ፈጨ​ሁት፤ እንደ ትቢ​ያም ሆነ፤ ትቢ​ያ​ው​ንም ከተ​ራ​ራው በሚ​ወ​ርድ ወንዝ ጨመ​ር​ሁት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች