Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 20:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በዕ​ድ​ሜ​ህም ላይ ዐሥራ አም​ስት ዓመት እጨ​ም​ራ​ለሁ፤ አን​ተ​ንና ይህ​ችን ከተማ ከአ​ሦር ንጉሥ እጅ እታ​ደ​ጋ​ለሁ፤ ስለ እኔ፥ ስለ ባሪ​ያ​ዬም ስለ ዳዊት ይህ​ችን ከተማ አጋ​ር​ዳ​ታ​ለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በዕድሜህም ላይ ዐሥራ ዐምስት ዓመት እጨምርልሃለሁ፤ አንተንና ይህችን ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፤ ስለ እኔ ስለ ራሴና ስለ ባሪያዬ ስለ ዳዊት ስል ይህችን ከተማ እከላከልላታለሁ።’ ”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በዕድሜህም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምርልሃለሁ፤ አንተንና ይህችን የኢየሩሳሌምን ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ በመታደግ አድናለሁ፤ ስለ ክብሬና ለአገልጋዬ ለዳዊት ስለ ሰጠሁት የተስፋ ቃል ከተማይቱን በመከላከል እጠብቃታለሁ።’”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በዕድሜህም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምርልሃለሁ፤ አንተንና ይህችን የኢየሩሳሌምን ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ በመታደግ አድናለሁ፤ ስለ ክብሬና ለአገልጋዬ ለዳዊት ስለ ሰጠሁት የተስፋ ቃል ከተማይቱን በመከላከል እጠብቃታለሁ።’ ”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በዕድሜህም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ፤ አንተንና ይህችን ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፤ ስለ እኔም ስለ ባሪያዬም ስለ ዳዊት ይህችን ከተማ እጋርዳታለሁ።’”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 20:6
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለ እኔም፥ ስለ ባሪ​ያዬ ስለ ዳዊ​ትም ይህ​ችን ከተማ እጋ​ር​ዳ​ታ​ለሁ።”


እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፦ ‘ጳው​ሎስ ሆይ፥ አት​ፍራ፤ በቄ​ሣር ፊት ልት​ቆም ይገ​ባ​ሃል፤ ከአ​ን​ተም ጋር የሚ​ሄ​ዱ​ትን ሁሉ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ንተ ሰጥ​ቶ​ሃል።’


ስለ​ዚህ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በጽ​ዮን የም​ት​ኖር ሕዝቤ ሆይ፥ ከአ​ሦር የተ​ነሣ አት​ፍራ፤ በበ​ትር ይመ​ቱ​ሃ​ልና፥ የግ​ብ​ፅ​ንም መን​ገድ ታይ ዘንድ መቅ​ሠ​ፍ​ቴን አመ​ጣ​ብ​ሃ​ለ​ሁና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕዝ​ቅ​ያ​ስ​ንና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ከአ​ሦር ንጉሥ ከስ​ና​ክ​ሬም እጅና ከሁ​ሉም እጅ አዳ​ና​ቸው፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ካለው ሁሉ አሳ​ረ​ፋ​ቸው።


ኢሳ​ይ​ያ​ስም አለው፥ “የበ​ለስ ጥፍ​ጥፍ አም​ጥ​ተህ በእ​ባ​ጭህ ላይ አድ​ርግ ትፈ​ወ​ሳ​ለ​ህም።”


ስለ እኔም፥ ስለ ባሪ​ያ​ዬም ስለ ዳዊት ይህ​ችን ከተማ እረ​ዳ​ታ​ለሁ አድ​ና​ታ​ለ​ሁም።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች