Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 17:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 እነ​ዚ​ህም አሕ​ዛብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈሩ ነበር፤ ደግ​ሞም የተ​ቀ​ረጹ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን ያመ​ልኩ ነበር፤ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም፥ የልጅ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም አባ​ቶ​ቻ​ቸው እን​ዳ​ደ​ረጉ እስከ ዛሬ ድረስ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 እነዚህ ሕዝቦች ምንም እንኳ በአንድ ወገን እግዚአብሔርን ቢያመልኩትም፣ የተቀረጹ ምስሎቻቸውንም ያገለግሉ ነበር። ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸውም አባቶቻቸው ያደረጉትን ዛሬም እንደ ቀጠሉበት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 እነዚያ ሕዝቦች በዚሁ ዓይነት እግዚአብሔርን ማምለክ ጀመሩ፤ በሌላ በኩል ግን ለጣዖቶቻቸው ይሰግዱ ነበር፤ ዘሮቻቸውም እስከ ዛሬ ድረስ ይህንኑ ዓይነት አምልኮ እንደ ቀጠሉ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 እነዚያ ሕዝቦች በዚሁ ዐይነት እግዚአብሔርን ማምለክ ጀመሩ፤ በሌላ በኩል ግን ለጣዖቶቻቸው ይሰግዱ ነበር፤ ዘሮቻቸውም እስከ ዛሬ ድረስ ይህንኑ ዐይነት አምልኮ እንደ ቀጠሉ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 እነዚህም አሕዛብ እግዚአብሔርን ይፈሩ ነበር፤ ደግሞም የተቀረጹ ምስሎቻቸውን ያመልኩ ነበር፤ ልጆቻቸውም የልጅ ልጆቻቸውም አባቶቻቸው እንዳደረጉ እንዲሁ እስከ ዛሬ ድረስ ያደርጋሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 17:41
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሰገነትም ላይ ለሰማይ ሠራዊት የሚሰግዱትን፥ በእግዚአብሔርና በንጉሣቸው በሚልኮም ምለው የሚሰግዱትን፥


“ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።


ኤል​ያ​ስም ወደ ሕዝቡ ሁሉ ቀርቦ፥ “እስከ መቼ በሁ​ለት አሳብ ታነ​ክ​ሳ​ላ​ችሁ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ቢሆን እር​ሱን ተከ​ተሉ፤ በዓ​ልም አም​ላክ ቢሆን እር​ሱን ተከ​ተሉ” አለ። ሕዝ​ቡም አን​ዲት ቃል አል​መ​ለ​ሱ​ለ​ትም።


ነገር ግን እነ​ርሱ እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጉት ልማ​ዳ​ቸ​ውን አት​ስሙ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች