Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 17:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሲፈሩ ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው እንደ ፈለ​ሱት እንደ አሕ​ዛብ ልማድ አም​ላ​ካ​ቸ​ውን ያመ​ልኩ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 በአንድ በኩል እግዚአብሔርን ሲያመልኩ፣ በሌላ በኩል ግን እንደየአገራቸው ልማድ የየራሳቸውን አማልክት ያመልኩ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 በዚህም ዓይነት እግዚአብሔርን ማምለክ ጀመሩ፤ በሌላ በኩል ግን ቀድሞ ይኖሩባቸው በነበሩት ሕዝቦች ይፈጽሙት በነበረው ልማድ መሠረት ለባዕዳን አማልክታቸው ይሰግዱ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 በዚህም ዐይነት እግዚአብሔርን ማምለክ ጀመሩ፤ በሌላ በኩል ግን ቀድሞ ይኖሩባቸው በነበሩት ሕዝቦች ይፈጽሙት በነበረው ልማድ መሠረት ለባዕዳን አማልክታቸው ይሰግዱ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 እግዚአብሔርንም ሲፈሩ ከመካከላቸው እንደ ፈለሱት እንደ አሕዛብ ልማድ አምላካቸውን ያመልኩ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 17:33
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኤል​ያ​ስም ወደ ሕዝቡ ሁሉ ቀርቦ፥ “እስከ መቼ በሁ​ለት አሳብ ታነ​ክ​ሳ​ላ​ችሁ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ቢሆን እር​ሱን ተከ​ተሉ፤ በዓ​ልም አም​ላክ ቢሆን እር​ሱን ተከ​ተሉ” አለ። ሕዝ​ቡም አን​ዲት ቃል አል​መ​ለ​ሱ​ለ​ትም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ይፈሩ ነበር፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ በሚ​ኖ​ሩ​በት ከተማ በሰ​ማ​ርያ በሠ​ሩት በከ​ፍ​ታው ቦታ ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አኖሩ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ይፈሩ ነበር፤ ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ለኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች ካህ​ና​ትን አደ​ረጉ፤ በኮ​ረ​ብ​ታ​ውም መስ​ገ​ጃ​ዎች ይሠዉ ነበር።


እስከ ዛሬም ድረስ እንደ ልማ​ዳ​ቸው ያደ​ር​ጋሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ይፈ​ራሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስ​ራ​ኤል ብሎ የጠ​ራ​ውን የያ​ዕ​ቆ​ብን ልጆች እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው ሥር​ዐ​ትና ፍርድ፥ ሕግና ትእ​ዛ​ዝም ያደ​ር​ጋሉ።


እነ​ዚ​ህም አሕ​ዛብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈሩ ነበር፤ ደግ​ሞም የተ​ቀ​ረጹ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን ያመ​ልኩ ነበር፤ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም፥ የልጅ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም አባ​ቶ​ቻ​ቸው እን​ዳ​ደ​ረጉ እስከ ዛሬ ድረስ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋሉ።”


ልባ​ቸው ተከ​ፈለ፤ አሁ​ንም ይጠ​ፋሉ፤ እርሱ መሠ​ዊ​ያ​ቸ​ውን ያፈ​ር​ሳል፤ ሐው​ል​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ያጠ​ፋል።


በሰገነትም ላይ ለሰማይ ሠራዊት የሚሰግዱትን፥ በእግዚአብሔርና በንጉሣቸው በሚልኮም ምለው የሚሰግዱትን፥


“ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።


ለሁ​ለት ጌቶች መገ​ዛት የሚ​ችል አገ​ል​ጋይ የለም፤ ካል​ሆ​ነም አን​ዱን ይወ​ድ​ዳል፤ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ይጠ​ላል፤ ወይም ለአ​ንዱ ይታ​ዘ​ዛል፤ ለሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም እንቢ ይላል፤ እን​ዲ​ሁም እና​ንተ ገን​ዘብ እየ​ወ​ደ​ዳ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መገ​ዛት አት​ች​ሉም።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች